ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 14

በአገራችን ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያኖች „…እመቤታችን ሆይ…“ የሚለውን የጸሎት መስመሮች ከካቶሊኮቹ ጋር ሁነው ጨምረውበታል። ከዚያ ወዲህ ወይም ከዚያም በፊት „…ክፋት እና መጥፎ ሥራን በደልንና ጭቃኔን መዋሸት እና ማታላልን“ አንድን ልጅ አባቶች ሲመክሩ ከዚህ ራቅ ከዚህም ተጠንቀቅ ይህን ከልብህ አውጣ …ተው“ ብለው ያስተምራሉ። ከክፋትና ከክፉ ሰው ከአረመኔና ከቀመኛ ከመጥፎ ሥራና ሃሳብ ከአጸያፊ ተግባሮች…ወላጆች ይህን ከሚያደርጉና ከሚመክሩ ሰዎች ቢቻላችሁ ራቁ እናንተም አታድርጉ በእንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ የተበከሉትን አጠገባችሁ አታድርሱ ብለውም ያስጠነቅቃሉ። „…ይመክራሉ ያስተምራሉ“ የሚለው ቃል የሰውን ልጅ ወደ ሚገራው ወደ ትምህርትና ወደ መልካም አስተዳደግ ወደ ወግና ወደ ሥርዓት ወደ ጥበብና ወደ ዕውቀት አንድን ሰው – በሕይወት ዘመኑ ኮትኮቶ የሚወስድ ተጨማሪ መንገድ እንዳለ ያሳያል። ይህን ተገንዝቦ ፕላቶ በሰው ልጆች ታሪክ (የአይሁዶች ትምህርት ቤት ነበር) የመጀመሪያውን አካዳሚ መሰረተ። በግሸን አምባ ሌላው የኢትዮጵያ መሣፍንት ልጆች ትምህርት የሚቀስሙበት አዳሪ ትምህርት ቤት -ይህን አንዳዶቹ እሥር ቤት ይሉታል- ተከፍቶ እዚያ ወጣቶች አስተዳደርና አነጋገር ነገር ማየትና ማገናዘብ ይማሩበት ነበር። ከዚህ ጋር-ቀደም ሲል- በርካታ ጥንታዊ ገዳሞች ትላልቅ በሁዋላ አገሪቱን የሚመሩና የመሩ ሰዎች የፈለቁበት ትምህርት ቤቶች ተቆርቁረው ተከፍተዋል ። በአክሱም ቤተ- መንግሥት በጥንታዊት ኢትዮጵያ የግሪክ አስተማሪዎች ~ 14 ~