ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 12

የሮሙ ቄሣር ኔሮ በዕብሪት ልቡ አብጦ – እሱ እራሱን አምላክ አድርጎ አይቶም ሊሆን ይችላል – እሳት ለኩሶ ከተማይቱን ሲያጋይ ሠገነቱ ላይ ቁጭ ብሎ ሙዚቃ እየሰማ እና ክራሩን እየተጫወተ ሰው ሁሉ ነፍሱን በዚያን ሰዓት ለማዳን ብድግ ብሎ ሲያመልጥ ከተማይቱዋም በዚያን ዘመን ያኔ ፈርሳ አመድ ሲትለብስ ትርምሱን እግሩን ዘርግቶ – በዘመኑ የነበሩት እንደጻፉት እና እንዳስተላለፉልን እሱ ከላይ ሁኖ እሱ እየሳቀ ግርግሩን ይመለከት ነበር። ለቀናት ለተራቡ አንበሳና ነብር ክርስቲያኖችን ወርውሮ እሱ በሌላ ጊዚያቶች እዚያው ኮለሲዩም ስታዲዮም ውስጥ -ዳቦና ጨዋታ ለተራው ሕዝብ በሚባለው ፍልስፍና- በአውሬዎች እነሱ ሲቦጫጨቁ እሱ ቄሣሩ ከትዳር ጓደኛዋ ጋር ወይኑን እየተዝናና ይጎነጭ ነበር ። ሳይናገር በአውራ ጣቱ ብቻ ይወስናል። ደስ እንዳለው አንዴ ወደ ላይ ወይም ወደ ታች በማሳየት በግላዲያተሮች ሕይወት እዚያው (ጠበቃ የለ) ፍርዱን ይሰጣል። አጃቢዎችም የእሱን ፊት እያዩ -ደስ ለማሰኘት አብረው ይስቁ ይሳለቁም ነበር። በአረመኔነቱ በታሪክ የሚታወቀው ኔሮ ብቻ አይደለም። አነጣጣሪ ተኳሾች አሉ። እሥረኛ ሲገርፉና ሲያሰቃዩ የማይከብዳቸው ሰዎች ብዙ ናቸው።ሲያዋክቡ ሲቆጡ የሚረኩ አሉ። አብዮታዊ እርምጃ ሌላው አስገራሚ ውሳኔ ነው ። ~ 12 ~