ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 42

ከዚህ አንጻር ሲታይ የወሃና የዳቦ….የልብስና የመድሓኒት የቤትና…. ጥያቄዎች የተቀበሩ ፈንጅ ቦንቦች ናቸው። አፍሪካ ደግሞ በተለይ መሪዎቹ ለነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ ሳትሰጥ እንደ አለፉት ዘመናት ነገሮችን ሁሉ ሸፋፍና እና አድበስብሳ ለማለፍ ከሞከረች/ከሞከሩ – ሌሎች ቦታዎች ተጽፎ አንደሚነበበውድብልቅልቁ አንድ ቀን መውጣቱ የማይቀር ነገር ነው። የሚፈልሱትን ስደተኞቹን አይተው ረሃብተኛውን ቆጥረው …ትርምሱ ተጀምሮአል በርካታ ጋዜጣዎች ወደ ማለቱ ተሸጋግረዋል። በተለይ በወሃ አጠቃቀም ጉዳይ ላይ ከአልተነጋገሩ ከአልተደማመጡ መፍትሔም በጋራ (ከአገርም ሰው ከጎረቤትም ጋር) ቁጭ ብለው ከአልተለሙ መተናነቅ ጋዜጣው እንደሚለው የማይቀር ነገር ነው። አብዛኛው ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የሰው ልጆች ዘር ሁሉ ቢቆጠሩ የሚኖሩት በወሃ ዳር ከእሱም በሚገኘው የእርሻ ምርት ነው። “ሰዎች ከአልተስማሙ በወሃ ጥያቄ ጦርነት መታወጁ የማይቀር ነው” የሚለው የጀርመኑ ጋዜጣ በደቡብ አፍሪካና በሊሶቶ በኖቤል ሽልማት ተሸላሚው በኔልሰን ማንዴላ አንዴ በታወጀው የክተት አዋጅ ታሪክ (ስንቱ ያኔ ይህን ዜና እንደሰማ አይታወቅም) በእሱ ይጀምራል። ደቡብ አፍሪካን የሚያጠጡ ጅረቶች የሚፈሱት ከሊሶቶ ተራራ የሚወርዱ ንጽህ ወሃ ናቸው። አንድ ቀን ሊሶቶ ወሃዬን እንደፈለኩት አደርጋለሁ ብላ የማንዴላን መንግሥት ለማሸበር አንድ ፕላን ጋዜጣው እንዳለው አውጥታለች። ይህም የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊውን ማንዴላን አስደንግጦ „…ወሃውን ልቀቂ አለበለዚያ የክተት ጦር ይከተላል“ የሚል ማስጠንቀቂያን ያስነሳል። በደቡብ አፍሪካ የተከበበቺው ሊሶቶ ከጀመረቺው ሓሳብ እራሱዋን ቶሎ ብላ ታርቃለች። እንደዚያው ለኢትዮጵያም ከግብጽ አንድ ቀን ማስጠንቀቂያ መምጣቱ የማይቀር ነገር ነው ብሎ ቪኪሊክስ ላይ አንዴ የተነበበውን ሚሥጢር ጋዜጣው ያነሳል። „…ኢትዮጵያን እንመታለን!“ያሉትን ዛቻ መልሶ ጋዜጣው ያስታውሳል። አሁን ብዙ ቦታ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሱዳን „በድብቅ መሬት ሸለመ /ሸጠ „ የሚባሉ ዜናዎችን በምናነብበት ሰዓት „ሱድ ዶች ሳይቱንግ “ የተባለው የጀርመኑ ጋዜጣ „የሱዳን መንግሥት ~ 42 ~