Test Drive April 2015 | Page 26

የተሜ ገጽ አንዲት ሀገር በጥበብ ብርሀን ከተመራች የድንቁርናን ከል ከላይዋ ላይ ገፋ ለመጣል አትቸገርም፡፡ ስለምን ቢባል ጠቢብ በበሀሪው በራስ ወዳድነት እግረ-ሙቅ ተጠፍሮ ዘመኑን ሁሉ በከርሱ ምሪት አይኖርምና ነው፡፡ ይልቁንም ጠቢብ ያለማሰለስ የነብሱን በሮች እያንኳኳ ገሚሱን ወደፊት ገሚሱንም የኋልዮሽ በርግዶ በዘመን መሀል ይመላለሳል፡፡ እናም ሲሻው ወደ ኋላ ሽምጥ ይጋልብና ስለትናንት ምን መሳይነት አንድም በቡሩሹ ዳሶ አሊያም በብእሩ ከትቦ እነሆ ይላል፤ በል ሲለውም በንስራዊ አይነ-ህሊናው እየተመራ ሀገሩን በዛሬዋ በረከትና መርገምቷ ላይ ሰይሟት ነገዋ ምን እንደሰነቀላት ያሳያታል፡፡ ታዲያ ይህን መሰሉን ኮኮብ ተከትላ የተመመች ሀገር ኋላቀርነትን ከመቃብር ዱላ የስልጣኔ ሰገነት ላይ ዙፋኗን ብታኖር የተገባ አይደለምን? በየትውፊቱም ሆነ ድርሳናቱ ሀገረ-ኢትዮጵያ የጠቢባን መፍለቂያ መሆኗ ተደጋግሞ ተመስክሮላታል፡፡ ፊታችንን የኋልዮሽ ብናዞር ቅዱስ ያሬድ በመቋሚያው ሰማይን እየዳሰሰ ዜማን ሲያሽሞነሙናት እናየዋለን፤እይታችንን ወዲህ ወደኛ ቀረብ እናድርገው ካልንም የህወይትን እረቂቅነት አፈወርቅ በብሩሹ ሲራቀቅባት፣ ጸጋዬ በቅኔ ሲፈታተናት፣ሙላቱ በሙዚቃ ተጠየቂ ሲላት፣