Test Drive April 2015 | Page 25

ራቁታቸውን ባይቀሩም የተበጣጠሰ የአረንጓዴ ድሪቶ ሆነው ይታያሉ፡፡ እንደ ችግር ሊጠቀሱ ከሚችሉ ነገሮች ውስጥ ዋነኞቹን እንይ ብንል ቅድሚያ ሰጥተን ማየት የሚገባን በእኔ እምነት ከልምዳችን ከተረዳነው አንጻር ወረተኛ ትጋታችንዋነኛው ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ የተተከሉትን ዕጽዋት ወደ ቆሻሻ ጥግ የመወርወር አባዜ ነው ፡፡ ለወረተኛ ትጋታችን የምንሰጠው መፍትሔ በተያያዥነት ለሁለተኛውም ችግር መፍቻ የመሆን አቅም ሊኖረው ይችላል ፡፡ ባ’ንድ ወቅት ለጋሽ አበራ ሞላ (ስለሺ ደምሴ) ዋና አዝማችና ፊትአውራሪ ሆነን የከተማችንን የጽዳት ጥበቃና አረንጓዴ የማልበስ ስራ አብዮታዊ ሊያስኝ በሚችል መልኩ ተሳትፎ ነበረን ፡፡ ከስራዎቹም እንጥቀስ ከተባለ ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ እንዴት አድርጎ ከቆሻሻ መጣያ ጥግነት ወደ መንፈስ ማደሻ አረንጓዴነት እንደቀየረው ማስታወሱ ይበቃል ፡፡ አሁንም ቢሆን ቦታውን ሄዶ በማየት የድሮውን እያስታወሱ ምን ያህል አስደሳች ስራ እንደሆነ መመስከር ይቻላል ፡፡ በወቅቱ አዲስ አበባ አራቱም አቅጣጫዎች ላይ የነበረው የጽዳትና የአረንጓዴነት ዘመቻ "የጋሽ አበራ ሞላ እምባ በከንቱ ፈሶ አይቀርም !" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረ መሆኑን እናስታውሳለን ፡፡ በየአካባቢው የተካሄዱ የጽዳት ስራዎች ምን ያህል አዲስ አበባችን የአርንጓዴ አብዮት ውስጥ ገብታ እንደነበር ማስረጃ ነው ፡፡ ግና ምን ያደርጋል የአንድ ወቅት የወረት ስራ ሆነና ተመልሰን እዛው አዙሪታችን ውስጥ ገብተናል ሌላ ጋሽ አበራ ሞላ መጥቶ እስከሚያለቅስ ፡፡