የሁሉንም ትኩረት የሚሻው የኑሮ ውድነት
ቅንድል ዲጂታል መፅሔት በቅንድል ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማህበር ወጣቶች ተዘጋጅቶ በ E-square አድቨርታይዚንግ እና ኢቨንትስ የሚቀርብ በማህበራዊ ፡ ስነ-ልቦናዊ እና ጤና ነክ ጉዳዮች ዙርያ የሚያተኩር ዲጂታል መፅሔት ነው ፡፡ የካቲት 2011 ተቋቋመ ፡፡
አድራሻ
(+ 251 ) 912178520 (+ 251 ) 920019699
e-mail- kdigitalmagazine @ gmail . com Telegram- @ KenDelM FaceBook- ቅንድል ዲጂታል መፅሔት Www . Ethiokindel . com
በሀገራችን ረጅምና አስቸጋሪ ግዜ ከወሰዱ የተለያዩ ፖለቲካዊ ለውጦች ጋር ተያይዞ የመንግስትም ሆነ የአብዛኛው ማህበረሰብ አትኩሮት ወደ ፖለቲካው ከሆነ ሰነባብቷል ። ምንም እንኳን ፖለቲካው ከኢኮኖሚም ሆነ ከማህበረሰባዊ ትስስር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ቢኖረውም የዕለት ተዕለት እሳቤና ድርጊታችንን በገዛው ፖለቲካ ሳቢያ ችላ እየተባለ ያለው ኢኮኖሚ አሳሳቢ ጀረጃ ላይ መድረሱን ብዙዎች ይስማሙበታል ።
ኢትዮጲያ ውስጥ በከተማ ብቻ ያለው ስራ አጥነት 30 ከመቶ ደርሷል ። የህብረተሰቡ የመግዛት አቅም እና የገበያው ሁኔታ እርቀቱ ያልተመጣጠነ መሆኑን ማህበረሰቡ በማማረር መግለፅ ከጀመረ ውሎ አድሯል ። በኢትዮጲያ ውስጥ የዋጋ ንረት እያሻቀበ መሄዱ የአደባባይ ሀቅ ሆኗል ፡፡ ወጣቱ በስራ አጥነትና ኢኮኖሚያዊ ልሽቀት ውስጥ መግባቱ ሀገሪቷ ካለችበት ችግር በተጨማሪ ሌላ እራስ ምታትን የሚፈጥር ነው ። ምንም እንኳን እኩልነት የሰፈነበት አካታች ፖለቲካ ወይም ፖሊሲ ከመንግስት የሚጠበቅ ወሳኝ ኩነት ቢሆንም ማህበረሰቡ በተለይም ወጣቱ የፖለቲካ ተሳትፎውን እውቀት ላይ በተመረኮዙና በተመጣጠኑ ተሳትፎዎች ላይ ብቻ በማድረግ የንግድ ፈጠራና የስራ ጥራት ላይ የበለጠ ማተኮር ይኖርበታል ።
ኢኮኖሚው ትኩረት ይገባዋል ። ወጣቱ የስራ መፍጠር አቅሙ ሊዳብር ይገባል ። በገንዘብም ሆነ ቀላልና ምቹ በሆኑ አሰራሮች መታገዝ እና መስራት አለበት ። ህብረተሰቡ የሚታመምበት የዋጋ ንረት ጥያቄ ጆሮ ሊያገኝ ይገባል ። በኢኮኖሚ እራሷን ያላደበረች ሀገር ሁሌም በልመና ውስጥ ናት ። የተቀረው ፖለቲካም ሆነ ሉአላዊነት በዚሁ ይፈተናል ። እያንዳንዱ ዜጋ ሰርቶ ለማደር ፤ ቆጥቦ ለመለወጥ ካልጣረ ለችግሩ መፍትሄ ማግኘት አይቻልም ።
ምንም እንኳን መንግስት ስራ ለመፍጠርና ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ጅምር ስራዎችን እየሰራ ቢሆንም የወጣቱን ሰርቶ የማደግ ፤ በልቶ የማደር መሰረታዊ ጥያቄ የፖለቲካው ሹኩቻ በሚያወጣው የጎላ ድምፅ መዋጥ የለበትም ። ማህበረሰቡ አሁን ላይ እየፈተነው ያለውን የኑሮ ውድነት የምንገራበት መንገድ ካላበጀን ፤ የዋጋ ንረቱን ካልገታን ፤ ወሰን የለሽ የነጋዴዎችን ፍትህ አልባ የንግድ ስግብግብነት ካላስቆምንና መንግስት እንደመንግስት ኢኮኖሚያዊ ተቋሟቱ ላይ ትኩረት አድሮጎ የፖለቲካ ወጣ ገባው የማይጎረብጣቸውና መልሰው ህዝቡን የማይጎረብጡ ተቋሟት መፍጠር ካልተቻለ ከፖለቲካው ባልተናነሰ ከባድ የኢኮኖሚ ፈተና ውስጥ መግባታችን ስለማይቀር መንግስትሞ ሆነ ማህበረሰቡ እንዲሁም ወጣቱ ኢኮኖሚው የሚገባውን አትኩሮትና ጥረት ሊሰጠው ይገባል ።
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 4