“ ሃብታሙን በቀደሙት መፅሐፎቹ ማለትም በአውሮራ ፣ የሱፍ አበባ ፣ እና ታላቁ ተቃርኖ እንዳገኘሁት የጠለቅ የኢትዮጵያ ታሪክ እውቀት አለው ። ስለ አንድ መሪ የግል ባሕሪያት ፣ ስለ አንዳንድ ታሪካዊ ምስጢሮች ለምሣሌ ስለ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ኢኮኖሚስት መንገድ እንደዚሁም ለአንድ አውሮጵዊት አገር እንዲመሰልል የሰጠው መረጃ ለእኔ አስገራሚ ነበር ። ከዚህም በተጨማሪ ደራሲው አጉራ ዘለል እንዲሁም ጥራዝ ነጠቅነት በፍፁም አይታይበትም ። በተቻለው አቅም ሚዛናዊ ለመሆን ይጥራል ። ታሪክንም ላለማዛባት ትልቅ ጥንቃቄ ያደርጋል ። ይህ የመጀመሪያው ብቃቱ ነው ። ሁለተኛው እና አስገራሚው ብቃቱ ደግሞ የልቦለድ ድንቅ ፀሐፊነቱ ነው ። ገፅ ባህሪያቱ ፣ የታሪኩ ፍሰት ፣ የሴራው መጥበቅ ፣ የመቼት አቀራረፁ ፣ ልብ አንጠልጣይነቱ ፣ ጭብጡ ( ከጭብጥም የኢትዮጵያ ታሪክ ) ምን አለፋችሁ በአጠቃላይ ድንቅ ነው ። የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ አስተያየት ።
ርዕስ ፡ አስኳላ ደራሲ ፡ ሀብታሙ አለባቸው የገፅ ብዛት ፡ 444 ዋጋ ፡ 250 ብር
የሐሽማል መጽሐፍ ደራሲ የኔታ ሊቀ ሊቃውንት ሊቀ ጠበብት ማዕበል ፈጠነ አሁን ደግሞ በሌላኛው ስራቸው “ ከርታታ ኮከቦች ” መጥተዋል መልካም ንባብ ይሆንላችሁ ዘንድ ተመኘን ።
ሐሽማል ከመሆናቸው በፊት የተዋነይን ውኃ መጠጣት ነበረባቸው ። ሁለቱ ተማሪዎች ከውኃዋ ከተጎነጩ በኋላ ሊቁ ፋሬስ አንድ ታሪክ መዘዙ ። “ እኔና ቀለሙ ተፈሪ ይችን ውኃ የጠጣን ቀን ደስታው ሊያሳብደን ደርሶ ነበር ። ቀለሙ ከወሎ ሲመጣ ገና ብላቴና ነበር ። ኪነ ጥበብ ከሚባል ብስል ተማሪ ጋር መጥቶ የተዋነይን የቅኔ መንገድ ቀጸለ ። ከዚያ በፊት የዋድላውን የቅኔ መንገድ በደንብ ያውቀዋል ። የኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መባቻ ቅዳሜ ቀን በባተበት የዓመቱ መጨረሻ ቅዳሜ ቀን ከውኃዋ አብረን ጠጣን ። ክስተቷ በዚያ ቀን ነበር ። ከዚያ በፊት ያችን የምሥጢር ቀን ስንጠብቅ ዓመታትን አሳልፈናል ። ደጅ ጥናታችን የወግ አልነበረም ። ሕይወትን ፍለጋ እንደእኛ የተንከራተተ የለም ። ከርታታ ኮከቦች ነበርን ። ከመጽሐፉ የተወሰደ ።
ርዕስ ከርታታ ኮከቦች ደራሲ ማዕበል ፈጠነ የገፅ ብዛት 443 ዋጋ 233 ብር
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 28