ዮናስ ኃ / ማርቆስ e-mail- lijyoha2 @ gmail . com
ርዕስ ወደ ኋላ ደራሲ ሊዲያ ተስፋዬ ዋጋ 120ብር
እልፍ ገጾች
አስታውሳለሁ የግቢያችን በር ላይ በቀለም ምልክት የተደረገብን ቀን የሆንነውን መሆን ። ሰፈራችን ሁለት ሳይሆን ሁለት የሆነበትን ያንን ክፉ አጋጣሚ ። የተመደቡብን የሞት መላእክት የሚፈርስና የማይፈርስ ፣ የሚቃጠልና የማይቃጠለውን ቤት በቀይ ቀለም ለይተው ካለፉ በኋላ ስንታመስ ዋልን ። ሐረር ለሲዖል ቀረበች ። ሞት የጠበቁት ቀን ቢመጣ ጥሩ ነበር ... አልሆነም ። ያለ እንቅልፍ ያለፈው ሌሊት ሌላ ብርሃን የለሽ ቀን ተክቶልን ሄደ ። አብዛኛዎቻችን ትርፍ የሌለው ደረቅ ምጥ አማጥን ። ቁርጠቱ ብርቱ ፣ ሕመሙም ጽኑ ነበር ። በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ነፍሳችን ከሳች ፣ ቆዳችን ጠቆረ ፣ ተስፋ የምናደርገው ነገር ሁሉ ከውስጣችን ሙጥጥ ብሎ አለቀ ። ከተፈጠርሁ ጀምሮ አስቤው ፣ ሊኖር ይችላል ብዬም ጠርጥሬ የማላውቀውን ፍርሐት አካል ለብሶ ያየሁት ያን ቀን ነበር ። የነገሩ አካሄድ እየታያቸው ሐዘናችንን የተካፈሉ “ አትፍሩ ! ለበላይ አካል ጉዳዩን አሳውቀናል !” እያሉ ያጽናኑን ጎረቤቶች ነበሩ ። በዛው ልክ ደግሞ የእነርሱ ደጅ ስላልተንኳኳ ብቻ እንዳላየ ፣ እንዳልሰማ ሆነው በዝምታ ያለፉም አልታጡም ። እንጥፍጣፊ ርሕራሄ ማሳየት አቅቷቸው ... መጥፋታችንን ለማየት የቸኮሉም ነበሩበት ። አልቀረልንም ... የሚቀጥለው ቀን ከሌሊቱ ዘጠኝ ሠዓት ገደማ ከአንድ ጎጆ የድረሱልኝ ድምጽ ተሰማ ። አገር ምድሩ ሁሉ እኩል ኡኡታውን ያቀለጠው ያህል ከኅሊናዬ የማይጠፋ ጩኸት ሰፈሩን ደበላለቀው ። እኔና ፋሲል ኩርምት ብለን ከተቀመጥንበት በድንጋጤ ተነስተን ሮጥን ። ዞር ብሎ ማየት የሚታሰብ ነገር አልነበረም ። ጀርባዬ እስኪበሰብስ ፣ ግንባሬ በላብ እስኪታጠብ ወዴት እየሄድን እንደሆነ ያልየለት ሩጫችን እልባት ያገኘው ባጋጠመኝ እንቅፋት ምክንያት ነበር ። ውልክፍክፍ ብዬ ተደፋሁ ። ቀድሞውኑ ልቤ በፍርሐት ስለተሸረሸረ መትረፌን ማመን አልቀለለኝም ። እንደሌለሁ እየተሰማኝ መኖሬ ግራ የሚያጋባ ስሜት ፈጠረብኝ ። ፋሲልን ተደግፌ ትንፋሼን ለመሰብሰብ እየሞከርሁ ...“ ከየት መጥታችሁ ነው ? ወዴት ናችሁ ?” አለን አንድ ወጣት ። እንደ እኛው ሰው ይሁን የሞት መልአክ መለየት የምንችልበት ሁኔታ ውስጥ ስላልነበርን ሁለታችንም መልስ አልሰጠነውም ። ትቶን እስኪሄድ ድረስ ደግመን ልናየውም አልደፈርን ። ብቻ በዚያች ሌሊት እንዲቃጠል ከተፈረደበት አንዱ የሆነው የእኛ ቤት በውስጡ ከነበረው ንብረት ጋር መታሰቢያው ጠፋ ። ሞትን በሩጫ ቀድመን ነፍሳችንን ማትረፍ ስለቻልን ራሳችንን ዕድለኞች አድርገን ቆጠርን ። በእርግጥም ዕድለኞች ነን ። መኖር ባይፈቀድልንስ ?
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከኣሏት የግዕዝ ቋንቋ ሊቃውንት እና ምሁራን ዋንኛው የሆኑና ታላቅ የሃገር ባለውለታ ናቸው ። በግዕዝ ቋንቋችን ዙሪያም የበርካታ መጻሕፍት ደራሲ ናቸው ። በዚህ መጽሐፍ ግዕዝ ለመማር የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የግዕዝ መጻሕፍትን ለማንበብ እንጂ በግዕዝ ቋንቋ ለመነጋገር ወይም ለመጻፍ ፍላጎት ኖሯቸው አይመስለኝም ። ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው ያንን መሰረታዊ ፍላጎታቸውን በግዕዝ መዝገበ ቃላት እርዳታ ለማርካት እንዲያስችላቸው ሆኖ ነው ። ግን እግረ መንገዳቸውን የቋንቋ ሂደት እንዴት እንደሆነ እንዲያዩ አልፎ አልፎ አንዳንድ ትችት ውስጥ እገባለሁ ። ግዕዝ ተማሪው ግዕዝንና አማርኛን ያንድ ቋንቋ ሁለት ቅርንጫፎች ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ምክንያቱን ሰው ሳይነግረው በራሱ ተመራምሮ እንዲደርስበት መንገድ አሳየዋለሁ ። ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ።
|
ርዕስ “ ግዕዝ በቀላሉ ” ከናሙና ድርሰቶች ጋራ |
|
|
ደራሲ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ |
|
|
የገፅ ብዛት 250 - |
|
|
ዋጋ - 200 ብር |
|
ቅንድል መፅሔት |
ቅንነት ድል ያደርጋል ! |
ገጽ 27 |