ቅፅ_2_ቁጥር_10 | Page 25

‘ ማደሪያ የሌለዉ ግንድ ይዞ የሚዞረዉ ’ ዓባይ ’ ለጂጂ ‘’ የማያረጅ ዉበት ፣ የማያልቅ ቁንጅና ’’ ነዉ ። አገዉኛ ዜማዋ እንኳ ሳይቀር ቋንቋዉን የማይናገሩትን የመማረክ አማላይነት አለዉ ። ‘’ አንተ ሀገርህ ወዲያ ( x2 ) ከወንዙ ባሻገር የእኔ ሀገር ከወዲህ ወንዙን ሳንሻገር ታዲያ ምን አለበት ያም ሀገር ያም ሀገር እስቲ ስምትልህ ስቀበር አንተ ልጅ ዛሬን ከእኔ እደር ’’ የፍቅር ረሀብተኛዋ የተዋበች ሳዱላ በሞቴ አትሂድ ትለዋለች ። ‘ አገራችን ’ እስከሆን ድረስ ያም ‘ ሀገር ‘ ያም ‘ ሀገር ’( ያም የእኔ ነዉ ይሄም ያንተ ነዉ ) ትለዋለች ። በ ’’ እኔን የራበኝ ፍቅር ነዉ ’’ ‘’
ጎጃም ያረሰዉን ለጎንደር ካልሸጠ ጎንደር ያረሰዉን ለጎጃም ካልሸጠ የሸዋ አባት ልጅ ለትግሬ ካልሰጠ እህህህ ..’’ እዚህ ጋ የገጣሚ ደበበ ሰይፉን ‘’ ከአክሱም ጫፍ አቁማዳ ’’ እንድናስታውስ እንገዳደለን ። ‘’ ትግራይ ላከ ወሎ ጋ አበድረኝ ብሎ አንድ ቁና ጤፍ ወሎም አፈረና የለኝም ማለት ..... ላከ ወደሸዋ ‘’ ሸዋ ወደ ሀረር ፣ ሀረርም ወደ ባሌ እንዲህ እንዲህ እያለ ኢትዮጽያን አዳርሶ አቁማዳው አክሱም ጫፍ ላይ ይሰቀላል ። ደበበ እንዲህ ይላል ፦ ‘’ እኔና ወንድሜ ሁላችን ሁላችን ከባዶ አቁማዳ ነው የሚዛቅ ፍቅራችን ’’
እኛ ኢትዮጵያዊያን እጦት ተጋሪ ገመናና ሸሻጊ ነን ።
ጂጂ መግነጢሳዊ በሆነዉ መረዋ ድምፅዋ ከብዙዎች ልብ የቀሩ ስራዎችን አበርክታለች ። እኔን የራበኝ እንጀራ እህሉ ፣ ወተቱ ወይ ጠጁ መስሏቸው ችግሬ ጭንቀቴ ምንጩ ያልገባቸው ያቺ ሰው ተራበች ሲሉ ሰማኃቸው ’’ ስትልም ራህቧ ፍቅር መሆኑን ታፀናለች ።
# እንደ መደምደሚያ ሁለቱም በየፊናቸዉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን በስራቸዉ ከማግዘፍም ባለፈ ከመለኮታዉ ጣልቃ ገብነትና ንትረክ ያልተላቀቀዉን ታሪካችንን በየራሳቸዉ ቀለም በቃላት ብሩሽነት በልባችን ፅላት ላይ ስለዋል / ቀርፀዋል ። ከበላይ ያለዉ የአጭር አጭር ዳሰሳ የሁለቱንም ከያኒያን አጠቃላይ ስራዎች ያልቀነበበ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በተጠቀሱት ግጥሞች ላይ ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማከል ለሚሻ ሙሉ ፈቃድ የሰጠ ነዉ ።
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 25