ሲሊም የኦሮሞ ፈረሰኞችን ገድል ያወሳል ። በዋሽንግተን ዊኒቨርስሲቲ የአፍሪካ ጥናት ተመራማሪው ፕሮፌሰር ሬይሞንድ ጆናስ ከጦርነቱ ሸሽተው የተመለሱ የጣሊያን ተዋጊዎችን ጠይቆ እንዳሳፈረው ‘ ፈረሰኞቹ እንደ ‘’ ጥቁር ደራሽ ወንዝ ነበሩ ’’ ይላል ።
ወይ ሳልለዉ ብቀር ያኔ እኔ አልሆንም እኔ ‘’ እያለም ለሚኒልክ የክተት አዋጅ አወንታዊ ምላሽ ለድሉ ጉልህ አበርክቶ እንዳለዉ ይመሰክራል ። እኔ እኔ የሆንኩት ‘’ የናኔዉ እኔ ’’( አባቴ ) ወይ በማለቱ ነዉ አይነት ዉስጠ ወይራነትም አያጣዉም ።
በአጠቃላይ የቴዲ ኢትዮጵያ ስነልቦና ካልነኳት የማትነካና ከተነካች ደግሞ የክተት አዋጅ አውጃ ህዝቦቿን ከዳር እስከ ዳር የምታሰልፍና ድልን የምትቀዳጅ ናት ። ቴዲ ‘’ በሼመደፈር ’’ አንድነትን በልህቀት የሰበከ እንደ ‘’ አልሞላም ኪሴን ’’ ያሉቱ ደግሞ ስራዎቹ የትዉልዱን ሞራል ለማነፅ የሚታትሩ ሆነዉ እናገኛቸዋለን ።
# የጂጂ ኢትዮጵያ
ለእንስት እምብዛም ቦታ ና ክፍል በሌለዉ የሙዚቃ እንደስትሪና ለእንዲህ ላሉት ጉዳዮች ባድነት ለሚያጠቃዉ እንዲሁም ልማዱ ካልዳበረ ማህበረሰብ ወጥቶ ሙዚቀኛ መሆን አዳጋችነቱ ሊካድ የሚችል አይደለም ። ጂጂ በ ነዛሪ ግጥሞቿ እና ጆሮ ገብ ዜማዎቿ በርካታ ጭብጦችን ዳስሳለች ። የጂጂ ኢትዮጵያ የሶስት ሺ አመት እመቤት ናት ።
‘’ እቴ አንቺ የእኔ ሙሽራ እስቲ ልጠይቅሽ ያገቡሻል ይፈቱሻል አሁንም ድንግል ነሽ ’’
ጥበባት
ምን ያለ ድንግልና በመገባት በመፈታት የማይገሰስ ? እመቤትነትና ሙሽራነትስ እንደምን ሰመሩ ? የኢትዮጵያን ረቂቅነት በቅጡ የተረዱ ዉብ ስንኞች ! ለጂጂ ኢትዮጵያ ‘’ የማንነት መለኪያ ፣ ኩራትና ክብር ’’ ናት ። # የጂጂ አደዋ ‘’ የሰዉ ልጅ ክቡር ሰዉ መሆን ክቡር ’’ በሚል የስንኝ መባቻ የሚጀምረዉ ይሄ ሙዚቃ የሰዉን ቦታ በተገባ ያብራራ ነዉ ። ‘’ ሰዉ ሞቷል ሰዉ ሊያድን ሰዉን ሊያከብር በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ ...’’ በጂጂ አደዋ ሰዉ ሊያድን ሰዉ ሞቷል ። ደግነት ክብር ና ፍቅር አስገድደዉት ነፍሱን ያለ ስስት በመስጠት የሞት ሲሳይ ሆኗል ። አጠቃላይ የሰዉ ልጆችን ታሪክ እስከወዲያኛዉ በተለይ ቀለም ተኮር ንቀትን የሻረዉ የአድዋ ድል በጂጂ ብዕር ሲገለፅ መሪሪ መስዋዕትነቱ የእልፎችን አጥንት ከፍሎ የደም ሀይቅ ሰርቶ የመጣ እንጂ የዋዛ ድል እንዳይደለ በምናብ አድዋ ድረስ በመዉሰድ ያሳየናል ። የጂጂ አደዋ ህማሙ አልቀረዉም ። የተከፈለዉ ሰዉ እንደሆነ ላቅ ባለ ግጥማዊ አቅም ይቀርባል ። ‘’ የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት ሰዉ ተከፍሎበታል ከደምና ካጥንት ’’
በማለት የተከፈለዉን መረሪ መስዋዕትነት ታነሳለች ። ‘’ አድዋ ዛሬ እናት አድዋ ትላንት መቼ ተነሱና የወዳደቁት ’’ ም ስትል የመስዋዕትነቱን ዘመን አይሽሬነትና ለትዉልዱ ቀና ማለት የወደቁ እንዳሉ እንዳይዘነጋ ታሳስባለች ። የጂጂ አድዋ ምስክር ነዉ ። የጀግኖች አባቶቻችን ተጋድሎ ምስክር ። የጦር አዉድማዉ ነፍስ ግብር እማኝ ። ሌሎቹ ፍፁም ኢትዮጵያዊ የሆኑ ዜማዎቿም አይጠገቡም ።
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 24