ቅፅ_2_ቁጥር_10 | Page 23

# የቴዲ አፍሮ ኢትዮጲያ

ጥበባት

የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ግጥሞች ወኔአምና ደም አሙቅ ናቸዉ ።
‘’ የሰለሞን ዕፅ ነሽ የቁድሳን ዕንባ ያበቀለሽ ቅጠል ዛሬ አዲስ አይደለም በለኮሰዉ እሳት የነካሽ ሲቃጠል ’’
እነዚህ ስንኞች የኢትዮጵያን ጥንታዊነትና የህዝቦቿን አልበገር ባይነት ይገልፃሉ ። ድምፃዊዉ ‘’ ፍቅር ያሸንፋል ’’ ባይ ቢሆንም የአንድ አፍቃሪ ታሪክ የሚተርከዉ ’’ 70 ’’ ደረጃ ሙዚቃዉ እንኳን ሳይቀር መውዜሩን አስቀምጦ ክራር ያነሳ ገፀባህሪ ነዉ ። በቅርብ ለጆሮ ባበቃዉ ሙዚቃዉም
‘’ እንኳን ለጎረቤት ከወንዜ ለጠጣ ቋያ እሳት ነዉ ክንዴ ከሩቅም ለመጣ ’’
አይነት ጀብዳዊ መልዕክት እናገኛለን ። ቴዲ ማህበራዊ እንግልታችንን ይሰቅቀዋል ።
‘’ አፈር ይዞ ዉስጡ አረንጓዴ ለምን ይሆን የራበዉ ሆዴ ?’’
ሲልም አንጡራ ሀብት እያለን ከድህነት አረንቋ እንዳልወጣን በቁጭት ይጠይቃል ።
‘’ ብራናዉ ይነበብ ተዘርግቶ ባትሮንሱ ላይ የነፋሲለደስ የነተዋናይ ’’
እያለ የስልጣኔ በኩር የነበርን ፣ የእድገት ማማ ላይ እንደነበርን ያወሳል ።
‘’ አንተ አበርሃም የኦሪት ስባት የእነ እስማኤል የይሳቅ አባት ልክ እንደክሱም ራስ ቀርፀሃት ራሴን በፍቅር ጣፍ ለኩሳት ነፍሴን ’’
ተማፅንኦዉ የሰዉ ልጅ ሁሉ ሊኖረዉ የሚገባን አማናዊ ፍቅር የሻተ ነዉ ።
የቴዲ ምናብ ለትላልቅ የታሪክ ድሎች ይሰግራል ። አሸናፊነት የሚመስጠዉም ይመስላል ። የነገር ሀቲቱንም የሚያዘግነዉ እንደ መቅደላ ፣ አደዋ ካሉ ቦታዎችና እንደ አፄ ቴዎድሮስ ፣ አፄ ሚኒሊክና አፄ ሀይለ ስላሴ ካሉ ሰብኦች ነው ። ቴዲ በታሪካ የሚመሰጥ ይመስላል ። አፍቃሬ አፄዎች ነው ብንል እሳሳት ይሆን ? # የቴዲ አደዋ በአመዛኙ የዉትድርና ዉሎአቸዉን የሚተርከዉ ይሄ ሙዚቃ ‘’ ባልቻ አባቱ ነፈሰ መድፉን ጣለዉ ተኩሶ ’’ መሰል ምስል ከሳችና ታሪክ ነጋሪ ስንኞች ያሉበት ሲሆን ግጥማዊ ጨመቁን ስንመለከት ውጊያዉን ተራኪ እና በድሉ ተማራኪ ሆኖ እናገኘዋለን ። ጀጀባdha ኢጆሌ ቢየኮ ዲናፍ ኢላዩ ኢትዮጵያ ‘’
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 23