ሕብረ፥ቅላጼ / SIDE ተፈላጊ ቁም፥ነገሮ/Attractors of Meanings&SOCIAL HARM | Page 19

እነዚህ አድማሶች የየራሳቸው ማዕከላዊ ምሶሶ / የሚስቡ፣ የሚወደዱ ልዩ ቁም ነገሮች/ አሏቸው። (ማዕካላዊ ምሶሶዎች፣ በሚያለያዩ ማሰተሳሰሪያዎች ይቀላጠፋሉ፣(Axes: “the disjunctive Syntheses” /2)) 1ኛ፣ ሰብዓዊነት (ሰ) 2ኛ፣ ስነ፥አይምሮ/ ንቃተ፥ሕሊና (ሕ) 3ኛ፣ ኪነት (ኪ) 4ኛ፣ መድረሻ፥ግብ (ግ) 5ኛ፣ ቁሳቁስ (ቁ/m) 6ኛ፣ ስነ፥ሃይል (ሃ/E) 7ኛ፣ ብርሃን (ብ/c) 8ኛ፣ ምንጩ (ም) ተመራማሪው አይንስታይን ስለ ስነ፥ሃይል፣ብርሃንና ቁሳቁስ ያገኘውን ማመዛዛኛ/ ፎርሙላ/፣ ባንድ በኩል፣ (በእግዚአብሄሩ ከፊለ፥ዓለም ውስጥ ብለን ለምንሰይመው) ለቁስ፥አካላዊውና ለመንፈሳዊው መስኮች ማመላከቻ አድርገን ብንወስደው፤ E=mc2 ; Energy = Mass x (Speed of Light)2 ቁሳቁስ፣በብርሃን ፍጥነት እጥፍ ጊዜ ቢባዛ፤ ስነ፥ሃይል ን ያክላል ብሎ መመዘን ይቻላል ማለት ነው። ሃ = ቁ *ብ *ብ በሌላ በኩል ደግሞ ፣ ለማህበራዊው ስነ፥ፍጥረ ት መገንዘቢያ ይሆን ዘንድ ፣ (የሰው፥ልጅ ሌላው ከፊለ፥ ዓለም ብለን በምንጠራው) ለማህበራዊውና ለባህላዊው መስኮች፣ ተመሳሳይ ማመዛዘኛ ማስቀመጥ ይቻል ይሆናል። I= hq2 ; Intelligence = Humanity x (Quality of Music)2 አንድ የሆነ፣ ሰብዓዊ የህሊና፥መመዘኛ (ሰ)፣ በስነ፥ ኪነት ረቂቅነት(ኪ) እጥፍ ጊዜ ቢባዛ ወይንም ቢገናኝ፤ ለስነ፥አይምሮ (ሕ) ከብርና ክብደት ማለካኪያ ይሆን ይሆናል ለማለት ነው። ሕ = ሰ* ኪ* ኪ በዚህ የአመለካከት ዘይቤ/ (model/ሞዴል)፣ የሕይወት ትርጉሙ፣ በአራቱ መስኮች መሃከልና በየራሳቸው በየመስኮዎቹ ውስጥ ሕብራዊነትን/ ሕብረ፥ቅላጼን እያስተናገዱ፣ በየመስክ፥ዘርፉ ያሉት ከፍተኛ የሰው ልጅ ዓላማዎች ላይ መድረስ ነው። እነዚህም፥ ሰላም፣ ሰብዓዊ ባህል፣ ፍጹማዊነት/ሃብት እና፣ ዕምነት ናቸው። እነዚህ ዓላማዎች የሚሳኩትን ያህል፣ ሕብረ፥ቅላጼውም፣ መለኮታዊው የሰው ልጅ ላይ፥ ማለትም መድረሻ፥ግቡ ላይ ደርሶ፣ ከምንጩ ጋር ለመግጠም ዝግጁ እንዲሆን ያደርገዋል። ዛሬ ያለንበት ዘመን ግን፣ አሳዛኝና እንዳውም፣ ጭራሹኑ፣ በፀረ፣ሕብራዊነቱ የተሞላ ነው። ይህ የዛሬው ዘመን የሚያሳዝን የሆነው፣ ፀረ፣ሕብራዊነቱ፣ በሕይወት መስኮቹ መሃከልም ሆነ በራሳቸው በየመስኮዎቹ ውስጥም ስለገነነ ነው። **** 1).Reformulated after an encounter with .complexity theory...and further philosophical survey (cf. Original intuition, 1/2006). 2) .Connective, conjunctive and disjunctive syntheses. Concepts from Kant, whitehead and Deleuze, as interpreted by Steven Shaviro, http://www.shaviro.com; and my fourth one, what I call reflective syntheses