ሕብረ፥ቅላጼ / SIDE Harmony 2014 | Page 12
ሕብረ፥ቅላጼ ሲነገር
*
ይሰምርለት ይሆን ሳይንስ ፍጹምነት
በአዲሱ አድማስ፣ ባየር፥ቦታ ሰዓት
ባህል እየሆነ ንፁህ ሰብዓዊነት፤
ታሪክ ሲገሰግስ፣ ላንድ አፍታ ቆም ሲል?
ለሰላም ነፃነት፣ ለአዲሱ ባህል!
ሕይወት እኮ ዕምነት ነው፣ ዕምነትም በሕይወት
ዝንተ፥ዘላለሙን፣ ከሰማይ፥ሰማያት፥
በሕብረ፥ቅላጼ ወደ ድለ፥ፋንታ፣ ዕፁብን ለማግኘት።
ዕ ል ል! ዕልልታ ነው የእርሱ ማሳረጊያው
በታላቁ ተስፋ፣ ምሕረቱ ነው ሕያው፤
ዕውነት ዕውነት በሉ፣ ምንጭ ይሰማዋል ሰው።
መልክተ፥ቅላጼ
HARMONY
ስነ፥ፍጥረት ሆነ ሰማየ፥ሰማያት
ሰው፥ልጅ ሲጥለቀለቅ በጥበቡ ሙላት
መንግሥት ታሪክ ሆኖ፣ ህጎቹ ነፃነት፣
ከዕምነት ከሃይማኖት
ንፁህ የሆነ ዕውቀት ለሚከሰትበት፣
ለመንግሥተ፥ሰማይ፣ ፍልሚያ እኮ ነው ሕይወት።
ለሰላም ለባሕል፣ ለፍጹማዊነት
ዕልል ዕልል እንበል፥ ለታላቁ ድርጊት!
በሕብረ፥ቅላጼ ለቅዱሱ ግብዓት
ምንጩን ይዳብሳል፣ ሰብዕ በመለኮት!