ለ አእምሮ / Le'Aimero የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳ | 页面 4

ነበር አይረሳም።ይህም ነገር ሳይሳካላቸው፣ እንደምናውቀው ቀርቶአል። ይህንንም በምኒልክ ላይ የተጀመረውን ዘመቻ(መቼ አቆመ) ከብዙ በጥቂቱ ትንሽ ቆይታችሁ ዘለቅ ስትሉ ትደርሱበታላችሁ። ምኒልክ እንግሊዝ አገር ለመጀመሪያ ጊዜ በ1900 ዓመተ-ምህረት መጀመሪያ ላይ የተካሄደውን „ የፓን አፍሪካ ጉባዔን በበላይ ጠባቂና በሊቀመንበርነት እንዲመሩ „ መጠየቃቸውን ዘግየት ብላችሁ እሱንም ዜና ታገኙታላችሁ። የምኒልክን መቶኛውን የሙት አመት ስናስታው ስለዚህ ንጉሥ ታሪካዊ ቦታውን ለመስጠትና ሙታንን የማስታወስ ባህል በአገራችንም እንደገና ተገቢውን ቦታ እንዲያገኝ-በማሰብነው። በእርግጥ „የሰማዕታት ቀን“ የሚባል በዓል ነበረን። ግን ስንቶቻችን ነን የሞቱትን ዘመዶቻችንን አፈር ከለበሱ ወዲህ ዞር ብለን የምናስታውሰው? ስለምኒልክ ዛሬ ስናነሳ „…ቅባቅ ዱሱን የተቀባ አንድ ንጉሥ ብድግ ብሎ አሁን ከገባንበት ጣጣ መጣጣ እሱ መጥቶ ያወጣናል „ለማለት አይደለም። እሱማ! እንኳን እሱና በአንድ በዞረበት ያልታወቀ ስም የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችም ለብቻቸው በ21ኛው ክፍለ ዘመን „ዕድሜ ልካቸውን የሚገዙበት“ የብልጣ ብልጥነት የአታላዮች የአምባገነን ሥርዓት የማይሆን የማይደረግ ነገር እንደሆነ ሁላችንም ገብቶናል። የጠፋው ዕወቀትና ብልሃት -እንዴት? የሚለው ላይ ነው። ምኒልክ „አገሬንና ሕዝቤን ለነጮች አሳልፌ ለባርነት አልሰጥም“ ያለ የዘመኑ ጀግና ሰው ነበር። ከአሁኑ ዘመን ከእኛ ትውልድ ደግሞ የሚጠበቀው ሌላ ነገር ሳይሆን እንደዚህ ዓይነቱን አመለካከትና የዲሞክራሲ መብቶችን ከዚሁ ጋር አብሮ የማስጠበቅ ቆራጥነት ነው። በአጭሩ እሱም ከአገር ነጻነት ጋር እኩል አብሮ የሚሄድ የግለስብ ነጻነትና የግለሰብ መብቶች መከበር ከሁሉም ነገር በፊት ይህን