ለ አእምሮ / Le'Aimero የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳ | Page 30

እንግዲህ እዚሁ የቤተ-መንግሥቱ አንደኛውና ትልቁ አዳራሽ- የመስተዋትአዳራሽ ውስጥ- ነው ከጥቅምት 11 እሰከ ጥቅምት 13 2013 ዓ.ም (እአአ) „ውርሰ ኢትዮጵያ“ የተባለው ድርጅት አሥራ ስድስተኛውን አመታዊ ጉባዔውን ጠርቶ፣ንጉሠ ነገሥቱን አጼ ምኒልክን ከሞቱ ከአንድ መቶ አመት በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የእኝህን ትልቅ ሰው ሥራና ገድል ያስታወሰው። ጉባዔውን የከፈቱት የከተማው ከንቲባ ሚስተር ክኑት ክሮይች እና የውርሰ ኢትዮጵያ ድርጅት የቦርዱ ሊቀመንበር ልጅ ዶ/ር አስፋ ወሰን አሥራተ ሁለቱም አንድ ላይ ሁነው እየተፈራረቁ ተራ በተራ በአደረጉት ረጅም ንግ