ለ አእምሮ / Le'Aimero የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳ | Page 28

መብት መከበር በተግባር ተዋግቶአል። በ ዘሥራ ዘጠነኛውና በሃያኛው ክፍለ-ዘመን በሰላም አልጋው ላይ የአረፈ የኢትዮጵያ ንጉሥ ማን ነው ቢባል ምኒልክ ብቻ ነው። ምኒልክ- በጎታ/Gotha ምን ይታወቃል በሰላማዊ ምርጫ ዘመን ፣ እኛም አንድ ቀን አራትና አምስት ጠቅላይ ሚኒስትሮቻችንን ከእነ ፕሬዚዳንቶቻችን (የክልል አይደለም) አብረን አቁመን አሰልፍን አንድ ቀን -እንደ አሜሪካና እንደ ጀርመን እንደ እንግሊዝና ፈረንሣይ እኛም እነጋብዛቸው ይሆናአል። እዚያ ላይ ለመድረስ ግን የብርሃን ፍልስፍናን ኢንላይትሜንትን አኝኮ መዋጥ ያስፈልጋል። ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደ ዳግማዊ ምኒልክ በዓለም የተደነቀ እንደ እሳቸው ደግሞ በአንዳንድ የአገሪቱ ልጆች 28 ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4 ዘንድ የተናቀ የአፍሪካ ንጉሥ የለም። ደፍረው -ይህ ይገርማል- ሐውልታቸው እንዲፈርስ አዲስ አበባ ላይ አንዳንዶቹ ጠይቀዋል። ብዙዎቹም ይህ የመታሰቢያ ሐውልቱ እንዳይነካ ታግለዋል። ለምልክትም ቀለም ጥቂቶቹ ቀብተዋል። በጀርመን አገር ጎታ በሚባለው ከተማ የመቶኛ የሙት አመታቸውን ምክንያት በማድረግና እሱንም በማስታወስ አሥራ ስድስተኛ „የውርሰ ኢትዮጵያ የሳይንስና የምርምር ጥናት ማህበር“ አመታዊ ጉባዔውን እዚያ አካሂዶ በንጉሠ ነገሥቱ በአጼ ምኒልክ ሥራና ገድላቸው ላይ ሦስት ቀን የፈጀ አተኩሮ ለእሳቸው ሰብሰባው ሰጥቶአል። ጎታ ታሪካዊ ከተማ ናት። እዚህ ነው የጀርመኑ የሲሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ የመጀመሪያውን የድርጅቱን ፕሮግራም ነድፎ ለጀርመን ሕዝብ ያስተዋወቀው። እዚህ ነው ከአምስት መቶ አመት በፊት እነ ዶክትር ማርቲን ሉተር የፕሮቴስታንትን ሃይማኖት እንቅስቃሴ በዘመናቸው ለኩሰው ይህን እምነት ሊያስፋፉ፣ሊያራምዱት የቻሉት። እዚሁ ነው ከሦስት መቶ ሃምሣ አመት በፊት ኢትዮጵያዊው አባ ጎርጎርዮስ እና የጀርመኑ ተወላጅ ሒዮብ ሉዶልፍ በቤተ መንግሥቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደገና የተገናኙት። 29