ለ አእምሮ / Le'Aimero የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳ | Seite 2
እምዬ እንደገና
ይ ዘ ት / Content
• ዳግማዊ ምኒልክ (ርዕስ አንቀጽ)
• ም ኒ ል ክ ና የአድዋው ድል
• ምኒልክ- በጎታ
ምኒልክ
በ
• አፍሪቃ! እንዴት ሰነበተች ?
ከኔልሰን ማንዴላ፣ ከዴሞክራቱ ጋ ር !
• ከኪነ ጥበብ ዓለም ፥
እሱንም ሁኔታ ወረድ ብላችሁ ትመለከቱታላችሁ።
„ጣይቱ „
ጣሊያኖች ሳይሆኑ በሁዋላ የተወለዱትና በታሪክ አጋጣሚ ሥልጣን ላይ የወጡ ወጣት
„ኢትዮጵያኖች“ የምኒልክን ሓውልት ከራስ መኮንን ጋር እናፍርስ ብለው ተነስተው እንደ
2
ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4
„ ብረት ቅርጫት ቀፎ የሮም ጎዳና ላይ ያንን የኢትዮጵያ ንጉሥ ነኝ የሚለውን ሰው ይዤ
እየጎተትኩ -ጥንታዊት ሮም በዚህ የታወቀች ናት- አመጥቼ አሳይችሁዋላሁ...“ ብሎ የፎከረው
ጄኔራል አደዋ ላይ ተቀጥቶ ወታደሩን በትኖ ሸሽቶ ነፍሱን ለማዳን አሥመራ ይህ ሰው
ገብቶአል። የአደዋን ጦርነት ለሚያውቁ ሰዎች ይህ አዲስ ታሪክ አይደለም።
አዲሱ ታሪክ አዲስ መሆን ያለበት እንዴት አድረገው ኢትዮጵያኖች ተስማምተው በጋራ
አንድላይ መላ-መተው የጣሊያንን ጦር አታለው ከምሽጉ አስወጥተው አውላላ ሜዳ ላይ
ደበደቡት የሚለው ብልሃት ነው። ለዚህም ነው የአደዋ ጦርነት በትክክል መቼ እና በስንት
ሰዓት ተጀመረ፣ ንጉሠ-ነገሥቱስ በዚያን ሰዓት የት ነበሩ የሚለውን ነገር በደንብ ለማስፈር
አስቸጋሪ የሆነው። ሰሚንም ነገሩ ግራ የሚያጋባው በዚህ ምክንያት ነው ።
3