ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 57
ትሆናለችሁ።“ የሚለውን ዓረፍተ ነገር ነውመርጠው በደብዳቤአቸው
ላይ አስፍረዋል።
„ጎሣ መለየት“ የሚለው ቃልም „የአውሮፓ መሣቂያ እንዳትሆኑ „
ከሚለው ጋርም በትክክል አብሮ ተቀምጦአል።
ደብዳቤው ለአሁኑ የሃይማኖት አባቶቻችንትላንት የተጸፈም ይመስላል።
ከእነሱም ጋር ወደውም ሆነ ሳይወዱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን ተገደው „ለተገነጠለቱም“ የኤርትራ ወንድሞቻችንና
እህቶቻችን አብሮም የተሰነዘረ ይመስላል።
በዚሁ ሳቢያም ከእነሱ ጋር አብረው (ሳይወዱ)ለሄዱት ለካቶሊኩም
ለውንጌላዊቱም፣ ለሞስሊም ሃይማኖት ተከታዮች ይመስላል።
አንድነት ተፋልሶ „እንደ ሽርሽር„የታየው „…መገንጠል“ ትዳር በብዙ
ቦታዎች አፍረሶአል። ቤተሰቦች በትኖአል። ልጆችን አለወላጅ ወላጆችን
አለልጆቻቸው አስቀርቶአል። ጦርነት ተከፍቶም ሥፍር ቁጥር የሌለው
ሰው ከሁለቱም ወገን ሞተዋል።… ተበትነው ለሄዱትም ወገኖቻችን
ደብዳቤው የተጻፈም ይመስላል።
ከሁሉም አሁን ቢሆን „ጌጥ“ እየሆነ ለመጣው ለዘር ክፍፍል አራጋቢዎች
ከመጥፎ ሓሳባቸው ቆጠብ እንዲሉና እንዲያስቡበት የተወረወረም
ማስጠንቀቂያ ይመስላል።
ጣይቱ „…ሳትቸገሩ እንዴት የድፍን አውሮፓ መሣቂያ ትሆናላችሁ“ ስሉ
በተዘዋዋሪ የአደዋን ድል ለካህናቶቹ መልሰው ማስታወሳቸው ነው።
ቀደም ሲል ኢትዮጵያኖች ተለያይተው ሳይሆን ተባብረው አንድ ላይ
ሁነው ተነስተው የውጭ ወራሪን መንግሥት ጣሊያንን ድል አድርገው
በዓለም ሕዝብ ፊት-በአውሮፓ ትልቅ አድናቆትን እንዳተረፉ እቴጌይቱ
በደንብ አዲስ አበባ ከተቀመጡ ልዩ መልዕክተኛ- አምባሳደሮች አፍ
በእነሱ በኩል ስለ እኛ ምን በውጭ አገሮች እንደሚወራ ጥሩ አድርገው
ያውቃሉ።
ለዚህም ነው ከአልጠፋ ነገር „…መሣቂያ“ አትሁኑ የሚለውን
መልዕክታቸውን ደብዳቤአቸው ላይ ያሰፈሩት።
57