ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 48
ወጣቱና ተተኪው ትውልድ እንደ አባቶቻቸውና እንደ እናቶታቸው
ቤተክርስቲያን መሄድ ሄዶ መጸለይ እነሱ ከአቆሙ ጊዜው ረዘም ይላል።
ጸሎት ለእነሱ መንፈስን ማደስ ሳይሆን ግዳጅ ይመስላቸዋል።መጽሓፍ
መድገም ስብከት መስማት የእግዚአብሔርን ቃል ማዳመጥ ንስሓ
መግባት እነዚህ ሁሉ -በእነሱ ዓይን -ጊዜው ያለፈበትና ከዘመኑ
ዕውቀትና ሥልጣኔ ጋርም አብሮ የማይሄዱ ነገሮች ናቸው ባይ ናቸው።
ከዚያም በላይ በሰበሰቡትና በአገኙት ዕውቀት „እግዚአብሔር የለም“
ከእነሱ መካከል የሚሉ ብዙ ናቸው።
ይህ ሁሉ አመለካከት ደግሞ በመጨረሻው ለቤተ ክርስቲያን
እንደወላጆቻቸውና እንደ አያት ቅድመ አያቶቻቸው በተራቸው ይህን
ከትውልድ ወደ ትውልድ ማስተላለፍ የሚገባቸውን ኃላፊነት „እምቢ …
ግብርም ለቤተ-ክርስቲያን አንከፍልም „ እነሱን ወደሚለው ውሳኔም
ወስዶአቸዋል።
„ቤተ-ክርስቲያኑን የምናስተዳድርበት ገንዘብ ቢኖረን „አስተዳዳሪው ቄሱ
እንዳሉት „…ይህኛውን ባልዘጋነውና ቢያንስ በአሉትና ከቀሩት ሰዎች ጋር
አብረን ተሰብስበን አንድላይ በየሳምንቱ እያስቀደስን በቆየን ነበር….“
ብለዋል።
ከአሜሪካን አገር የመጡ አገር ጎብኚዎችና የሉተር ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ተከታዮች ጀርመን አገር ሲመጡና የጀርመንን ምዕምናን
ሲመለከቱ „….ለመሆኑ እምነቱ የት ደረሰ ?“ብለው ሁሌ ያገኙትን ሰው
እዚህ ይጠይቃሉ።
በእርግጥ የቀድሞው የምሥራቅ ጀርመን ኮሚኒስት መንግሥት
ሃይማኖትንና ቤተ ክርስቲያንን አጥላልቶ ብዙዎቹን ተከታዮች አዳክሞ
ቤተ ክርስቲያኑዋን በጉልበቱና በፕሮፓጋንዳው ኦና ለማድረግ ብዙ
ጥረት አድርጎአል።
48