ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 38

ይችላሉ- ግን እሱ ብቻ ነው ለኢትዮጵያ መፍትሔው ወይም እኔ ብቻ ነኝ መፍትሔውን የማውቃው ብለው ሲሟገቱ ከአገኘን- እንደዚህ እያሉ የሚተናነቁ ናቸው - ( ለአገሪቱ ለኢትዮጵያ ችግር ስታሊን ሆነ ማርክስ እሰከ አሁን ድረስ ምንም ዓይነት መፍትሔ አላመጡም)- ተገቢውን ትችታችንን እንሰነዝራለን ። የኤርትራ፣ የኦሮሞ የትግሬ፣ የኦጋዴን ….ጥያቄ ያለ ስታሊን ቲዎሪና ያለ ማርክስ እና ሌኒን ያለ ማኦ ትምህርትና አይዲኦሎጂ ስማቸውን እየቀያየሩ መጥተው ደጋፊ አባልና ተከታይ ጀሌ መሰብሰብ እንደማይችሉ አንስተን በየጊዜው እንደዚህ ዓይነቱ ጨዋታ ወደፊት መልክ እንዲይዝም እንጥራለን። በስታሊን ቲዎሪ በማርክስ ትምህርት በሌኒን እና በማኦ አይዲኦሎጂ የትም ቦታ የትም አገር፣-የታወቀውን ለመድገም- የትም አህጉር ጤነኛ መንግሥት እንዳልተገነባ በየጊዝው እናነሳለን። ቻይናንን የሚጠቅሱልን አሉ። ኪዩባን የሚጠሩ። ወይም እስከነአካቴው ደፍረው አንዴውኑ ሰሜን ኮሪያን የሚጠቅሱም ከመካከላችን አይጠፉም።ግን በእነዚያ መንግሥታት ሥር ሰበአዊ መብቶች ይከበራሉ? ለመሆኑ ሕዝቡ መሪዎቹን መምረጥ ይችላል? ነጻ-ጋዜጣ ነጻ ኢንተርኔት አለ? ሰው በሰላም አለ ሰላይ የልቡን መናገር ይችላል? እላይ በተጠቀሱት ሰዎች ትምህርትና ፍልስፍና ሥር „ሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች፣ በእነሱ አይዲኦሎጂ ሥር የትም አገር-እንደገና የታወቀውን ለመድገም- በሥራ ተተርጉሞ እንዳልታየ፣እንዳልመጣ ፈጽሞ እንዳልተከበሩ ወደፊት በተከታታይ በሚወጡት „የካሲዮጵያ ማህደር“ ላይ እንመላለስበታለን። ከሃምሳ አመት በላይ ሁለት ትውልድ ያንኑ መልሶ መላልሶ (ገዢዎቹ እነማን እንደሆኑ ግልጽ በሆኑበት ዘመን) እንደ ማስቲካ መፈክሮችን ማኘክ- ነጮቹ እንደሚሉት በያፍዝ አደንግዝ የመንደር ጨዋታ ጊዜአችንን ማጥፋት ጨርሶ ተገቢ አይደለም። ነገሮች መቋጠር አለባቸው። 38