ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 19
ነው። እንደ መጠለያ ድንኳንና ጎጆም ያገለግላቸዋል። ለአንዳዶቹማ
እንደ „ቤተሰብም“ ነው። እንደ ዔሊ ቀፎ ጠንካራ ምሽግ በቀላሉ
የማይሰበር ዛጎል ይመስላቸዋል። እንደ ጃንጥላም ሁኖ ከሚርከፈከፈው
ዝናብና በትንሹ ከሚፈነጥቀው የጸሓይ ጮራ ለጊዜው ይከላከላል።
ከአልተጠነቀቁ አዲዮሎጂ አእምሮን ሰልቦ „ባሪያ“ አድርጎ የሕልም ዓለም
ውስጥ ከቶ አፍዝዞ ጦር ሜዳ ድረስ ይነዳል። አውሎ ንፋስ ሲመጣ
ኃይለኛ ማዕበል ሲነሳ ደግሞ በቀላሉ ተኖ በመጣው ፍጥነት ተመልሶ
ይጠፋል። ያ ሲሆን ደግሞ በኤርትራና በጠቅላላው ምሥራቅ አፍሪካ
እንደምናየው ሰው ሁሉ ግራ ተጋብቶ ለካስ ያ ሁሉ ድካም ለዚህ ነው
ብሎ ለስደት ይዳረጋል። ወይም ጆሮውን ዘግቶ ጀርባውን አዙሮ
ይተኛል።
በደንብ ለመመልከት ሁለቱን ጀርመኖች እንውሰድ: – ምዕራቡንና
ምሥራቁን ጀርመን!
ለምንደው ጀርመኖች የዛሬ ዘጠና አምስት ገደማ ንጉሡን አባረው
የቫይመሩን ሪፓብሊክ አውጀው „…እኔ ልግዛ እኔ ልምራ“ በሚባለው
የፓለቲካ ድርጅቶች ንትርክ ውስጥ ገብተው ያ እፎይ ብሎ ለመኖር
የሚፈልገውን ሕዝብ በአንዴ በነገር አሳክረው በቀላሉ ሊያወናብዱት
የቻሉት?
ለምንድነው አብዛኛው የጀርመን የፖለቲካ ድርጅት በዚሁ በቫይመር
ሪፓብሊክ ዘመን የራሱን ተደባዳቢና ተዋጊ ጦር ልዩ መለዮ የወታደር
ልብስ የማዕከላዊ ኮሚቴ የስለላ ድርጅት የቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ክፍል
ፈጥሮና መሥርቶ መንገድ ላይ እርስ በእራሱ መፋለጥ የጀመረው?
እንግዲህ እንዴት ነው ሒትለር በጀርመን አገር አሸናፊ ሁኖ ሊወጣ
የቻለው?
ለምንድነው ከፋሽሽቱ ሒትለር አገዛዝ በሁዋላ
ጀርመን ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በሁዋላ፣
ለሁለት ይህች አንድ አገር የተከፈለቸው?
ለምንድ ነው – አንደኛው ኮሚኒስት
ሁለተኛው ነጻ -የዲሞክራቲክ ሕብረተሰብ
19