ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 14

በዚያች አንዳንዶቹ ትክ ብለው መልስ ለመስጠት በሚያስቡበትና በሚያሳስሉበት ሰዓትና ደቂቃ ከየት እነደመጣች የማይታወቅ አንዲት ጥንቸል ሽው ብላ ታልፋለች። ስታልፍ ከሩቁ ያዩ ሁለት የስብሰባው ተሳታፊዎች ተጠቃቅሰው ብድግ ብለው በዚያ በረጃጅም እግሮቻቸው ወደፊት እየተሳቡና እየተገፋተሩ „…እሱዋማ የእኔ ናት። የለም የአንተ“ እየተባባሉ ማሳደድ ይጀምራሉ። የት እንደገቡ ሳይታወቅ:- ቢጠበቁ እነሱ ሳይመለሱ በዚያው ጭልጥ ብለው ጠፍተው ቀርተዋል። እነሱ ተረስተው:ወይይቱ እንደገና በሌላ ጥያቄ ይከፈታል። ያም ገና በደንብ ሳይደመጥ በመካከሉ አንዲት ተንኮለኛ እነሱን ውሾቹን በማነደድ ብቻ ደስታውን የምታገኝ ቅምጥ የሳሎን ድመት ተደብቃ ቀስ ብላ ጠጋ ብላ በጭረዋ የአንዱን ውሻ ጀርባ ገረፍ አድርጋ ፈትለክ ብላ ትሰወራለች። እሱና አጠገቡ የነበሩት ውሾች ተደፈርን ብለው ብድግ ብለው ዘለው በተራቸው እሱዋን ድራሹዋን ለመጥፈት ሲዘሉ -ሥራዋን በደንብ ታውቃለች- አፈትልካ በመጀመሪያ ዘላ ግንቡ ላይ ከግንቡ ጣራው ላይ ጉብ ብላ „ሚያው“ እያለች እየተንጎራደደች እነሱ የተሰበሰቡበትን ዓላማ ረስተው የተለመደው ጩኸት ውስጥ ይገባሉ። በጩኸት ቅላጼ በእሱዋ ምክንያት ስብሰባው ሊፈርስ ጥቂት ይቀረዋል። እንደተለመደው ጮኸው ሲሰለቻቸው ይረጋጋሉ ብላ ንቃቸው ግቢዋ ውስጥ ዘላ ገብታ እመቤትዋ እግር ሥር በረንዳው ላይ ጋደም ትላለች። ደፍሮ ከመካከላቸው አንድ ጎልማሳ ውሻ ብድግ ይልና „…እኔ ከእናንተ በዕድሜ ወጣት በመሆኔ እምብዛም ብዙ ነገር አላውቅም። አሳዳጊዎቼ ፈረንጆቹ እኔን እዚህ ሜዳ ላይ ጥለው ወደ አገራቸው ከመመለሳቸውና ከመሄዳቸው በፊት እንደአየሁትና እንደተገነዘብኩት እነሱም በደጉ ዘመን እንዳሳደጉኝ እኔም በደንብ እንደአዳመጥኩት የፈረንጅ ውሾች ትምህርት ቤት ተልከው እዚያ ‚ሁሉን ዓይነት የአብሮ መኖር ሥርዓት‘ እነሱ እንዲማሩ ይደረጋል።… የማናውቀው እንግዳ እንኳን ወደ ቤታችን 14