ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 12
ሀ
…ምንድንነው እነሱ ያላቸው ችሎታና ብልሃት እኛ ደግሞ የሌለን
ነገር?“ ብሎ አንድ ውሻ እሱ እራሱ የሚያውቃቸውን ጋብዞና ጠርቶ
ዛፍ ሥር እነሱንምሰብስቦ አጠገቡ የቆሙትን የመንደር ውሾች
„…አንዲት መልስ ብቻ ከየትም አምጥተው ለጥያቄው እንዲሰጡት“
ያፋጥጣቸዋል።
ከፊሉ ውሻ -እዚያ ከነበሩት ውስጥ- ብዙውን ክፉና ደጉን በአለፉት
ቀናትና ረጅሙ አመታት ከእሱ ጋር አብረው የተካፈሉ የዕድሜ አኩዮቹ
ናቸው።ሌሎቹ አብሮ አደጎቹ ናቸው። የተቀሩት ልጆቹና የልጅ ልጆቹ
ናቸው። ሁሉም ጠባዩን ስለሚያውቁት መልስ ለመስጠት ተጨንቀዋል።
ብዥ ብሎበት አይኑን ከጎለጎለና ክራንቻ ጥርሱን አሳይቶ የጀርባው
ጠጉር ከተነሳ ማንም አይችለውም። ይቦጫጭቃቸዋል።
ከእነሱም ጋር በዚያን ዕለት ከተገኙት ውስጥ የቆየ መንደራቸውን ጥለው
– ስለፈረሰ የተቀላቀሉ ወዶ ገብ አዲስ መጤዎችም አሉበት። ትናንሽ
ቡችሎች ራቅ ብለው -የዚህች ዓለም ነገር ወዴት እንደምታመረ ገና
ያልገባቸው፣ ጮርቃ ምኑንም የማያውቁት እዚያ አፈሩ ላይ እነሱ
ይተረማመሳሉ ፣ በሆዳቸውም ይገለባበጣሉ።
ፍቅረኞቹም ሲተያዩ ይሽኮረመማሉ።መጪውን ቀን ክፉ ይሁን ወይም
በአለው ይቀጥል ወይም ደግሞ ደህና ይሁን የሚያውቅ ከእነሱ መካከል
የለም።
አውራው ግን የገባው ይመስላል።
„…ምንድነው እነሱ የተካኑበት ጸጋ ለእኛ ደግሞ ሥውር ሁኖ የማይታየን
ነገር? „ እስቲ ንገሩኝ እያለ ውሻው ይንጎራደዳል።
የእንስሶችንና የአውሬዎች ፋቡላ ታሪክ በደንብ ለተከታተለ አንድ ሰው
ከእነሱ ብዙም ባይሆን ትንሽ ትምህርት ይገኝበታል ይባላል ።
ታሪክ የማይረሳቸውናየሚያስታውሳቸው አሉ።
12