ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 40

ይህን ጥያቄ ለመመለስ „ጥላቻ“ ከየት ይመጣል? ብሎ እራስን መጠየቅ ያስፈልጋል። ንቀት፣ቅናት፣ክፋት …እነዚህ ሁሉ ከየት ይመጣሉ ብሎ መመራመርን ይጠይቃል። እንደዚህ ዓይነቱ መፈቃቀርና አንድነት መተማመን በሰዎች መካከል እንዳይመሰረት „ልዩነትን“ ብቻ ጥዋት ማታ የሚያስተምሩ ክፉ ሰዎች፣ አክራሪ በአገራችን እንደሚባለው „ቀስቃሽ ካድሬዎች“ በመካከላችን እንዳሉም መረዳት ያስፈልጋል። እንደዚህ ዓይነት ሰዎችደግሞ-ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን የትም ቦታ አሉ። እኛ ጋ ግን ልቅ እያጣ መጥቶአል። መድሓኒቱ ታዲያ ምንድነው? መድሓኒቱ አንድ ነገር ነው። በልዩነት ፋንታ አንድነትን ማስተማሩና የሰበአዊ መብቶችን ጥያቄ ከፍ አድርጎ ማንሳቱ ከፋፋዮችን – ይህ ነው ብልሃቱና ዘዴው እነሱን መቆሚያ ያሳጣቸዋል። በተለይ በጨለማ ሳይሆን በግልጽና ብርሃን በሚፈነጥቀው በጥበብና ዕውቀት ላይ ተመርኩዞ በጋዜጣ ላይ መወያየቱ። ፯ የሰለጠነ ዘመናዊ ሕብረተሰብ ከሃይማኖትና ከዘር ልዩነት ከዚያም በአሻግር አንድ የሚያደርጉትን እሴቶች ፈልጎ አግኝቶ በእሱ ላይ ጠንክሮ በመሥራት ብዙውን የውስጥ ችግሮቹን (ያለህበትን አካባቢ ተመልከት)በቀላሉ እሱ ፈቶአል። እንግዲህ በትክክል እንደሚታየው እያንዳንዱ የአገሪቱ ዜጋ ኃላፊቱን አይቶና ተገንዝቦ ቆርጦ ለእራሱና ለቤተሰቦቹ ለጎረቤቱና ለእናት አገሩ የተቻለውን አስተዋዕጾ – በብዙ አገሮች እንደምናየው- ለማበርከት የቻለውም ነጻ ሕብረተሰብ ውስጥ ለመተንፈስ በመቻሉ ነው። ያኔ ነው ሠራተኛውና ነጋዴው አስተማሪውና ሐኪሙ ተማሪና ገበሬው እንጂነሩና አናጢው…. አገሬ ሐብቴ መሬቴ አየሬ ብሎ ለእናት አገሩ ያለው ፍቅር የሚጠነክረው። መተማመን በሰዎች መካከል የነገሮች ሁሉ መሰረት ነው። በነጻ ሕብረተሰብ ውስጥ ደግሞ ሁሉ ነገር ሳይሸፋፈን ግልጽ ስለሆነ ሰዎች 40