ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 31

የድመት ግልገሎችንም ሰብስቦ ወሃ ውስጥ ዘፍቆ መግደል በሕግ ይህ እርምጃ እንደወንጀል ታይቶ ሰውዬውን ወይም ሴትዮዋን አያስቀጣም። በሌላ ቋንቋ ይፈቀዳል። አይጦችን በመርዝ አሳዶ እነሱን በየጊዜው የማይፈጅ ወሃ አጠራቃሚና ወሃ አቅራቢ ድርጅትና ግለሰብ እሱ ደግሞ ኃላፊነቱን አልተወጣም ተብሎ ተከሶ በሌላ በኩል በአገሪቱ ሕግ ይቀጣል። እንደዚህ ዓይነቱን እርምጃና ኃይል ጉልበት መጠቀም በሠለጠነው ዓለም የግድ (ዲክታተሮች የማንንም ፈቃድ የፓርላማን አባሎች ውሳኔ እንኳን አይጠብቁም) ሌጋሲውን ይህን የሚፈቅድለት ልዩ – ፈቃድ ከተሰየመው ክፍል ማግኘት ይኖርበታል። በቅርቡ እዚሁ ጀርመን አገር „…አደራ የተሰጠህን የሰው ውሻ በመስኮት ወርውረህ ገድለኻል“ ተብሎ አንድ ሰው ፍርድ ቤት ተከሶ ቀርቦ -አቃቤ ሕጉ የስድስት ወር እሥራት ጠይቆአል- ሰውዬው ተሟግቶ ከስድስት ወር እሥራት እንደምንም ብሎ ሊያመልጥ ችሎአል። „…አብሮ ለሚኖር ለማንም የአገሪቱ ዜጋ“ እነሱ -በዚህ አቀራረባቸው ማንኛውንም ተንቀሳቃሽ ፍጡር ይጨምሩበታል ይህ ነው እኛንም ነገሩን እንድናነሳ የገፋፋን- „ …በሰላም በዚህች ምድር ላይ ለመኖር የሚገባውንም መብቱን ለእያንዳንዱ – ለጋማና ለቀንድ ከብት ለሚጋልቡት ፈረስ፣ ለልጆቻቸው ለሸለሙት እንስሳ ጭምር አለ ገደብ መብታቸው ይከበር “ የሚለውን ጥያቄ ሌሎቹ ፈላስፋዎች እንደ Peter Carruthers ያሉ ሰዎች ከብቶች እንደ ሰው ልጆች አርቆ ማሰብና ለመጪና ለወደፊቱ ጊዜያቶችና ችግሮች ፕላን አውጥተው እቅዶች ዘርግተው አንዳች ነገር በዚህች ዓለም ላይ መሥራት ስለማይችሉ ይህ „የእኩልነት መብት ይሰጣቸው“ የሚባለው ነገር ቦታ የለውም ባይ ናቸው። ያም ሆኖ በእነሱ ላይ የሚካሄደውን ጭካኔ ይቃወማሉ። I የት ሊወስዱን ፈልገው ነው ? ምን እኛ የማናውቀውን ነገር ሊያስተምሩን አስበው ነው ይህን የመሰለ ጉዳይ አሁን የሚያነሱት?… ቅንጦት ነው ወይስ ጥጋብ ? ለመሆኑ ይህን…የእንስሳን መብት ማወቅ 31