ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 30

ግን እንዲሚባለው ና እንደሚገመተው- አንዳንድ አንባቢም ሰው በዚህች ደቂቃ እየሳቃ እንደሚያስበውና እንደሚናገረው ከብዙ ቦታም እንደሚሰማው – አብዛኛዎቹ እላይ የተጠቀሱት ነጥቦችና ጥያቄዎችፈላስፋዎቹም ያነሱት ፍሬ ሐሳቦችም ዝም ተብለው የሚታለፉ ቀላል ጉዳዮችና ነገሮች አይደሉም። H በከብቶችና በእንስሳ ላይ ምን ማድርግ እንደሚቻል በሕግ ወይም በሃይማኖት ወይም በዘልማድ የተፈቀዱና የተከለከሉ-እንደምናውቀው ሕግጋትና ደንቦች አሉ። አንዱ እንደ ጻፈውና ማንም አእምሮ ያለው ሰው እንደሚገምተው የጎረቤትን ዶሮ ሠርቆ ወይም ቀምቶ አርዶ በጀርመን አገር ሆነ ወይም በሌላ ቦታ መብላት ያስቀጣል። እንደዚሁ የጎረቤትን ውሻን ወይም ድመቱን ጠልፎ ወስዶ ይዞ የእሱን ጆሮ ወይም ጭራውን ወይም ደግሞ እግሩን መቁረጥ ክልክል ስለሆነ ይህም ያስቀጣል። ይህን ያደረገ ሰው እዚህ ሆነ ሌላ ቦታ ይቀጣል። ምናልባት እነደዚህ ዓይነቱ የከብት ስርቆት ድፍረት ሌላ ቦታ ጦር እሰከ ማማዘዝ ድረስም ያስኬዳል። በሌላ በኩል ሕግ አውጪው እራሱ ዝም ብሎ አይቶ የሚያለፋቸውም ነገሮች አሉ። በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ጀርመን አገር -እዚህ እንደተጻፈውከሚፈለፈሉት ከብዙ ሚሊዮን ጫጩቶች ውስጥ ወደ 50 ሚሊዮን የሚጠጉትን ወንድ ጫጩቶች ከሴቶቹ ለይቶ ለቅሞ እነሱን (እንቁላል ስለማይጥሉ ወይም እነሱ ቶሎ እንቁላል በየቀኑ እየጣሉ በቀላሉ ሰለማይደልቡ )በመርዝ ጢስ መፍጀት የዶሮ አርቢ ከበርቴውንም ገበሬውንም ይህን በማድረጉ ፈጽሞ አያስቀጣውም። 30