ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 28

የተቀመጡትን የቻይና እና የሩሲያን መንግሥታት -ይህን ቢያንስ ማለት እንችላለን – „ – ደር ሽፕግል የተባለው የጀርመኑ መጽሔት የቀድሞውን ቻንስለር ሔልሙት ሽሚትን ጠቅሶ እንደጻፈው[iv]- „በዚህ ሰበአዊ መብት መከበር አለበት በሚባለው አጉል ቀልድ እነሱን አናሰልቻቸው አናስጨንቃቸው ።“ ምን ዓይነት ዓለም ውስጥ ነው እኛ ለመሆኑ ያለነው? እነሱስ ነጮቹ ምንስ ዓይነት ሕይወት ውስጥ ነው የገቡት?… ይህን ለማለት ምን ነካቸው? ምን አሳሰባቸው? ምንስ አቅብጦአቸው ነው? እንደዚህ ዓይነቱ የክርክር ውስጥና ደረጃ ላይ እነሱ የደርሱት? ለመሆኑ እኛንስ ምን ነካን? በዚህ አቀራረባቸውና አመለካከታቸው ለመሆኑ ምን ይህል ጥለውን ሄደዋል ? በአንድ በኩል የከብቶችን ነጻነት! በሌላ በኩል በመጽሓፍ ቅዱስና በቅዱስ ቁራን በግሪክ ፍልፍስና እና…በሌሎቹ ሥልጣኔዎች „…ሰበአዊ መብት የሚባል ነገር የለም…“ የሚባልበት ነገር? እንደዚህ ዓይነቱን አሰተያየት በመስማታችንና በማየታችን እጅግ በጣም ተደንቀናል! ጉዳዩን ዛሬ የምናነሳውም -ግልጽ ለመሆን – ለዚህና በነዚሁ ምክንያት ብቻ ነው። G በአውሮፓ ሆነ ወይም በሌላም ቦታና አካባቢ በዚህ ዓለም ስለ እንስሳና ስለ ከብት ስለ አውሬና ስለ አዕወፋት ስ