ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 27

በዚህ በያዝነው 21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም እንደ አለፉት አመታትና ጊዜያት (እኛ ገና)„…ዲሞክራሲ በገደብ!… የለም ዲሞክራሲ አለገደብ፣ ዲሞክራሲ ለጭቁኑ ሕዝብ ብቻ… ዲሞክራሲ ለቡርጃውም!… የለም ለእነሱ መሰጠት የለበትም / …ለአንተም አይገባህም፣ለእሱ ጓደኛዬ ይገባዋል፣… ለዚያ ግን ጨርሶ አይሰጠውም !“ በሚባልበት ጊዜ እነደዚህ ዓይነቱ ጉዳይ እዚህ አውሮፓና እዚያ አሜሪካ የምዕራቡ ዓለም መነሳቱ በጣም አስደንቆናል። አስገርሞናል። ለመሆኑ እንደገና ለመጠየቅ የት ነው ያለነው? በየትኛው የአስሰተሳሰብ ክፍለ-ዘመን ውስጥ ነው እኛ የምንገኘው? “…. ጠባይህ…ታይቶ ትንሽ እንደ ሁኔታው ለአንተም ለእሱም ዲሞክራሲ ረጋ በል አንድ ቀን ይሰጠኻል/አይሰጥም„ በሚለው ንትርክ ዙሪያ ገብተን እንደ ዓይነ ስውር ሰዎች በዚህች ዓለም ውስጥ ስንወናበድና ስንከራተት „…የከብቶች መብት“ ይባስ ብለው „የእነሱ መብት አለአንዳች ጥያቄ ይጠበቅ…ይከበር „ እዚህ አውሮፓ እዚያም አሜሪካም በሚባልበት ጊዜ ጥያቄው ዛሬ መነሳቱ እኛንም በአንድ በኩል አስደስቶናአል፣ በሌላ በኩል ዕውነቱን ለመናገር ግራ አጋብቶናል። እሱ ብቻ አይደለም! ሌሎች ሓሳቦችም ከዚሁ ጋር እዚህ ይሰማሉ። F „…ሰበአዊ መብትን አስመልክቶ – ግልጽ ለማድረግ- በመጽሓፍ ቅዱስ ላይ ምንም ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የተጻፈ ነገር አናገኝም።በእስላም ሃይማኖት ውስጥም ይህን ጉዳይ የሚያነሳ መልዕክት እንደዚሁ ፈልገን አናይም። ምን ጊዜም የትም ቦታ የሰበአዊ መብት መከበር ጉዳይ ላይ ላቲን አሜሪካ ይኖሩ በነበሩት በኢንካ ሥልጣኔ ዘመን ይህ ጥያቄ ትልቅ ሚና በምንም ዓይነት አልተጫወተም። እዚያው አካባቢ ሰፍረው በነበሩት በቶልቴክን ወይም በአስቴክን ወይም ደግሞ በጥንታዊ ግብጾች ሥልጣኔ ጊዜ ከእናካቴው በግልጽ ለመናገር በጥንታዊ ግሪኮችም አልፈን ሄደንም በሮማዉያኖች ዘንድ ይህ የሰበአዊ መብት ጥያቄ የትም ቦታ እንደ ትልቅ ቁም ነገር አልተቆጠረም ።… ስለዚህ ሞስኮና ፔክንግ 27