ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 26

እሱንም አንስተው ወደ ፖለቲካ ዓላማቸውና ጥያቄአቸው እሱን ለማስተዋወቅ ይቸኩላሉ። ለሆዳችን ሲባል ይህን ያህል ሕይወት ይጥፋ ወይ? ብለው እራሳቸውንም አንባቢውንም ይጠይቃሉ። ሂላል ሴስዝጊን የእራሱዋ መልስ አላት። „ ምህረት የተደረገላቸው የእንስሶች ገነት„ በሚለው መንደሩዋ ሰፊ የገበሬ ቤትና ሜዳ ገዝታ በጉንም ላሙዋንም ዶሮ እና ፍየል ውሻና ድመቶችን ሰብስባ „ነጻነት ሰጥቼአቸዋለሁ „ብላ እነሱን „ሳትበላ“ ሴትዮዋ ትቀልባቸዋለች። የጀርመን ቀሳውስቶችና ካህናት አንድ ጊዜ ተሰብስበው የክርስቶስን ልደት ሲያከብሩ „እነሱም ከብቶቹ አምላካቸውን ማመስገን አለባቸው በሚለው