ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 15

ታጅበው በተቋሞች ታጥረው ሽንጎ ውስጥ ተመርጠው ሲላወሱ ብቻ ነው። ያኔ ደግሞ ኢትዮጵያ የማንም ሳትሆን የዘጠና ሚሊዮን ኑዋሪዎቹዋ የጋራ ቤትና ሐብት ናት።ኤርትራም እንደዚሁ። ከዚህ ውጭ በየጊዜው የዘርና የጎሣ የብሔር /ብሔረሰብ ጥያቄ እያነሱ ሰውን ማጋጨት በሕግም ፊት በታሪክም በሞራልም ያሰጠይቃል። በዓለምም በኢትዮጵያም „ …ልዩ የሆነ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ አዲስ ጎማ„ ፈረንጆቹ አጉል የሆነ ግራ የሚያጋባ የሚያስቅ ፍልስፍና አንዳንድ ሰዎች ሰንዝረው መጫወት ሲቃጣቸው እነሱ የሚናገሩትን ነገር እንደገና ለመድገም- „…አዲስ የትም ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የሚሽከረከር ጎማ ለመፍጠር እንዲያው አትድከም“ ይላሉ። ጊዜህን ወርቅማ ጊዜህን በሌላ ቁም ነገር ላይ እባክህአውለው ይላሉ። ነገ ?! ከሣቴ ብርሃን – ለአእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር-7 15