ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 52

አልክ?“ ብለው የሚቀልዱ ናቸው።ወደ ሰባው መጨረሻ ላይ ቀስ እያለ ብቅ ያለው ከሰማንያው ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ የተደራጁበትን ቤት እየጣሉ ወደ „ነጻ-አውጪዎቹ „ እየፈለሱ የገቡትን ሰዎች ሰውዬው እንደጀመረው በቦታው ላይ ነበሩ ማስተዋወቁን ቀጠለበት። ቆይቶ በአርባ አመት ውስጥ ስንት ጎዳና ያ የተማረ ሰው ሁሉ እንደተጓዘ ይተረክ ጀመር። ለመሆኑ ከዚህ ሁሉ ድካም በሁዋላ… ምን አገኘን? ተባለ። ….ምን አተረፍን? ለመሆኑ ለአገራችን ምን ሰራን? የትስ ደረስን? የት ነው ቀልጠን የቀረነው? …ስንቱ ሞተ? ለምንስ ሞቱ?… እገሌ አሁን የት ነው ያለው? የሚሉ ጥያቄዎች ተነሱ።በመጨረሻውስ ኢትዮጵያ ምን አገኝች? ተባለ።…ለዚህ ሁሉ ጥያቄና መልስ ፍለጋ ምሽቱ እንዳለ በውይይት ፉት ብሎ አለቀ። አንድ ፈረንጅ ሲቀልድ „ኢትዮጵያ- ኤርትራ በመገንጠሉዋ- በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ሁለት ድምጽ ያላት አገር በአሁኑ ጊዜ እሱዋ ብቻ ናት“ ብሎ የቀለደብን ነገር ተነሳ። እነሱም ይህ በተባለላቸው ማግስት ማንም እንደሚያውቀው ጦር ተማዘው ተዋጉ። ይህ ደግሞ ሌላ እራሱን የቻለ አርእስት ሁኖ ተከፈተ። መቼም እንደ ኢትዮጵያኖች “ክርክር” የሚወድ ሕዝብ የለም። የቆየ ባህላችን ነው። ዱሮ ሥርዓት ነበረው። አሁን… ነገ የመርከብ ሽርሽር እና የበርሊን አጥር ጉብኝት ዝነኛው የኦለምፒክ ስታዲዮም አዳራሽ… ፕሮግራም ስለአለን በጊዜ ብንተኛ ሲባል ሰው ሁሉ ተቃወመ። ከዚህ ሁሉ አመት በሁዋላ ወይኑ እየተቀዳ ማን ይተኛል! ቀልዱ መጣ። ዘፈን ተዘፈነ። ግጥሙ ወረደ። የዱሮ ታሪክ ተነሳ።አለ ጣጣመንጣጣ የምንሄድባቸው ዳንስ ቤቶች የተማሪ ማህበር ጉባዔ በበርሊን ከተማ በትልቁ ስታዲዮም በዚያን ጊዜ በተለኮሰው የክፍፍሉ ዘመን የነበሩ ነገሮች ሁሉ ተጠቀሱ። የፌደረሼሽን መቋቋም የአውሮፓ ~ 52 ~