ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 50

ከነበሩት ሴቶች ውስጥ ለአንዱዋ ዕድል ሰጥቶ እነሱን በማስተዋወቁ ቀጠለ። እነደገና አንደኛዋን እሷ አጠገብ የተቀመጠቺውን ዘሎ እንግዳ አስተናጋጁ „…ያ ደግሞ „ በጣቱ እያሳየ „…የቀድሞውን የዘውድ አገዛዝ የኃይለ ሥላሴን መንግሥት አልጋውን የኢትዮጵያ መፍትሔ እሱ ነው እያለ ፊት ለፊት ይደግፍ ነበር…“ የሚለውን ሰው ጠቆመ። „የተማሪዎች ስብሰባም ስንሄድ ቆይ `ዋጋሽን` አንድ ቀን ታገኚአለሽ እያለ ይዝትብን ነበር…“ እያለ የጠረጴዛው ግራና ቀኝ የተቀመጡትን በስማቸው እየጠራ ሲያስተዋውቅ በመካከሉ አንድት ቁንጅናዋ በምንም ዓይነት ከዚህ ሁሉ ዘመን በሁዋላ ያልከዳት ሳቂታዋ ወይዘሮ…ሴት ልጅዋን አስከትላ ሳሎን ውስጥ ገብታ ጠቅላላ አተኩሮውን በሁለት ደቂቃ ስባ እሱዋ እራሱዋ እንግዳ ሳትሆን ቤተኛ ሆና ያ ጎደለ ይሄ ቀረ ማለት ጀመረች። ዱሮውንም በቀልጣፋነቱዋ እወዳት ነበር። በፈገግታዋና በጥቅሻ ያኔ በርሊን ስትመጣ አንገታችንን የምታዞረው ልጅ አሁን ቤቱን በአንዴ ተቆጣጠረች። ይዛት የመጣች ልጅዋ ከመቅላቱዋ ሌላ (አባቱዋ ፈረንጅ መሆን አለበት)ቁርጥ እናቱዋን ነው። እሱዋን ማስተዋወቅ አያስፈልገኝም ብሎ ወደ“ አናርኪስቶቹ“ ወደ ሰሜን ኮሪያኖቹ ወደ ቼና ወደ ካስትሮ „ተከታዮች „ ከእነሱም ጋር ወደ ሁለቱ „አልባኒስቶቹ“ ፊቱን አዞረ። እንጂነሮችና መሓንዲሶች ነበሩ።ቄሶችና ዲያቆኖች ተገኝተው ነበር ። እነሱ ዝም ብለው ይህን ጉድ ይህን ታሪክ እየጠጡ ያዳምጣሉ። „እሱ አቶ…የማሪያምና የክርስቶስን ሥዕል ግድግዳው ላይ ሰቅሎ ሲጸልይ እነ እገሌ የማርክስና የሌኒን የስታሊንና የ…ፎቶዎች የቤት ግድግዳቸው ላይ ይሰቅሉ ነበር“ አለ።„ እሱ ድርሳነ ሚካኤልን ሲያነብ እኛ ማርክስ …“ ሲባል ሁሉም ይስቃሉ። ~ 50 ~