ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 46

ጠረጴዛው ላይ ከለተለያዩ አበባዎች ጋር የተለያዩ ፍራ ፍሬዎች መሶቡ ላይ በመልክ በመልካቸው ተቀምጠዋል። ብርቱካን ሎሚ ፓፓያ ማንጎ አናናስ መደሪን የወይን ዘለላ ሙዝ ፕላም ሸሪ ሮማንና …ከየት እንደመጣ አይታወቅም ትርንጎ ተዘርግተዋል። በፈላ ዘይት-ድስት ውስጥ የተጠበሱት ከዚያ ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። ክብ የአናናስ ቀለበቶችና ለሁለት ከመሓከሉ የተሰነጠቁ ሙዞች የፈላው ዘይት ውስጥ ገብተው ቀለማቸውን ቀይረዋል። በሁዋላ የማር ወለላ ፈሶባቸዋል። ከርሸም ሲሉና ከሞቀው ማሩ ጋር አፍ ውስጥ ሲፈሱ ግሩም ናቸው። ይህን ቀምሶ ነው አንዱ „ይህማ ያስኮራል! በአገራችን „የጠፋው ዲሰርት አለ እንዴ?“ ያለው። ትንሽ እሳት የመታው ሽንኮራም ሞቅ ብሎ ተቆራርጦ ቢመጣ አልጠላም አለ ሌላው።ጥርስ ቢኖር አይደለ? …ከሳቅ ጋር አለሦስተኛው። „ጥንቅሽ ብትል አይሻልም?“ አለ ሌላው።አይስክሪም ለሚፈገልጉት በሞቀ እንጆሪና ቀይ የቡና ፍሬ የሚመስል ሸሪ በተገመሰ ሮማንና በመንደሪን በኮክና በጥቁር ወይን ፍራ ፍሬዎች አንድ ላይ (እነዚህ ሁሉ ኢትዮጵያ ይበቅላሉ) በጎድጓዳ ሳህኖች ተዘጋጅተውና አሸብር