ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 38

የሆቴል እና የቡና ቤት ባለቤቶች ነጋዴና ተማሪዎች…ሐኪምና ወላጆች ሁሉም በሰውዬው ሥራ -ቱርኮቹ እንደሚሉት ተደስተዋል። በአስቸጋሪ ዘመን በመጥፎና መከራ ጊዜ ሰዎች አንድ መሪ ጠንካራ ክንድ ያለው መሪ ቢመጣላቸው ይፈልጋሉ።ይመኛሉ። እንዲመጣላቸውም ይጸልያሉ። በጥንታዊት ግሪክ የጦር ስልት የሚቀይስ ቀይሶም ሠራዊቱን የሚመራ አንድ „ቆራጥ የጦር መሪ ጀግና:- ፊታውራሪ“ ፈልገው ይሾማሉ። እሱም ሳያስቡት ተገለባብጦባቸው በአንድ ሌሊት ተቀይሮ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ አናታቸው ላይ ሊጨፍርም ይችላል። ይህን ከአዩ ደግሞ እሱን ያኔ እነሱ አይለቁትም። ሮምና ሮማውያን „በየት መንገድ“ እንደሚኬድ ፣ችግርም እንዴት እንደሚፈታ፣ ከመከራ የሚያወጣቸው ሰው… ለሠራዊቱም ለሕዝቡም „መንገድ የሚያሳይ መሪ“ እነሱ „ዲክታተር“ ይሉታል (የጊዜ ገደብ ሰጥተው) ከአገኙ እሱን ሰይመው እሱን ይከተሉታል። ሳት ቢል ከመንገዱ ወለም ዘለም ከአለ ዩሊየስ ሴዛርን እንዳደረጉት አጋድመው ያርዱታል። እሱም እነኔሮና ሌሎቹ ቄሣቹ እንዳደረጉት አልሰማ ብለው „ያፈነገጡትን ይዞ ይፈጃቸዋል!“ የነገሥታቶችስ ሥራ እንዴት ነው? እነሱ “በቅባ ቅዱስ” ይጨርሱታል። ቤኒቶ ሞሰሊኒ በ1925 አጋማሽ ላይ „ዱቼ“ „መሪ „ የሚለውን ሹመት እሱ እራሱ መርጦ አናቱ ላይ ደፍቶአል። እሱን አይቶ አዶልፍ ሒትለር „ደር ፊውረር“ ያው መሪአችን ብለው ተከታዮቹ እንዲጠሩት ትዕዛዙን አስተላልፎአል። „መለኮታዊነቱን“ እየዘላበዱ እንዳያበላሹበት አብሮ አደጎቹን ከአጠገቡ ተራ በተራ ጠራርጎ ገድሎአቸዋል። የጆርጂያው ተወላጅ የሩሲያ ኮሚኒስት ፓርቲው መሪ – እሱም ጓደኞቹንና አብሮ አደጎቹን ከአገጠገቡ በጽዳት ዘመቻ ቀስ በቀስ ከጠራረገና ከጨረሰ ወዲህ „…አባት! የአገር ሁሉ አባት!“ የሚባለውን ቅጽል ስም ትከሻው ላይ ለጥፎ ሁሉንም ጭጭ አድርጎአል። የኪዩባው ካስትሮ „ማክሲሞ ሊደር:- ታላቁ መሪ“ የሚለውን አጠራር መርጠዋል። ሳዳም ሁሴን „ተተኪ የሌለው መሪ“ እራሱን ሲያሰኝ „ወንድማዊ መሪ“ የሚለውን ጥሪ ኮነሬል ሞአመር ጋዳፊ መርጦ ለእራሱ ብቻ አድርጎአል። ~ 38 ~