ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 37

ነው ብሎ አሁን መናገር አይቻልም። ግን ነገርን ለመረዳት ዓለምን በሌላ ዓይን ለማየት ታሪኩ ይሰጣል። በሙስና እና በዘመድ ሥራ „ከእነ ቤተሰባቸው ተጨማልቀዋል “ ተብለው በብዙ ሰዎች ዘንድ የተከሰሱሱት የቱርኩ ጠቅላይ ሚንስትር በምን ተአምር ይሁን በምን- እንተርኔቱንም ዘግተውም ስልክም ተቆጣጥረው – እሳቸውና ድርጅታቸው ያ ሁሉ ሆኖ „በሕዝባቸው ድጋፍ “ በ45% እንደገና ተመርጠዋል። በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ አጭበርብረዋል የሚሉም አልጠፉም። ከክሪም ወዝግብ በሁዋላ ፕሬዚዳንት ፑቲን „በሕዝባቸው“ ዘንድ ያልተጠበቀ ድጋፍ እሰከ 70% ድረስ አግኝተዋል። ምንድነው ምክንያቱ? ምንድ ነው ? …የሰዎችን ፍላጎትና የልብ ትርታቸውን አንዴ ከፍ የሚያደርገው ሌላ ጊዜ የሚያሸፍተው ነገር? ሰዎችን እጃቸውን ይዞ ጥቅጥቅ ከአለ ጫካ፣… ሰው ከማይደርስበት በረሃ እና ከገደል አፋፍ ወይም ከሚነድ እሳትና ከመከራ ከጥፋትና ከውድቀት እነሱን ጎትቶ የሚያወጣቸው „መሪ“ ከሙሴና ከአሮን ታሪክ ወዲህ እነሱ እንደ ሚሹ እንደሚፈልጉ እንደሚመኙ ብዙዎቻችን በደንብ እናውቃለን። በሕዝብየተመረጡት ሙርሲ እሥር ቤትተወርውረውፊልድ ማርሻል አዚዚ መለዮአቸውን አውልቀው የግብጽ ፕሬዚዳንት ለመሆን ሲነሱከዚያየተላለፈው “የድጋፍ” ሥዕል ያስደነግጣል። አከታትሎ ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑ የሞስሊም ወንድማማቾች”የሞት ፍርድ”በግብጽተፈረዶባቸዋል። ሰዎች ምንድነው የሚስቡት? ከሚካኤል ጎርባቾቭ እና ከባሪስ ዬልሲን ከሶቪየትም መፈረካከስ መበተን ወዲህ ቪላዲሚር ፑቲን መጥተው „ጸጥታና ሰላምን የደስታን ዘመን የሩሲያ ታላቅነትን አድሳለሁ“ ብለው እንደተነሱ – ይህ አዲስ አይደለም ብዙዎቻችን ቀደም ሲል ሰምተናል። ታይፔን ኤርድዋን በኢስታንቡል የከተማው ከንቲባ በነበሩበት ዘመን ከተማውን ከወንበዴዎችና ከቀማኞች እጽድተዋል፣ የወሃ ቧንቧ ዘርግተዋል ደስ ሲለው የሚበራውንና የሚጠፋውን የከተማውን መብራት ገመዱን አድሰው ሰውን ከማታ ጨለማ አውጥተዋል። ~ 37 ~