ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 30

አንደኛው የፍልስፍና የምርምርና -የሳይንስ ጥናት መንገድ ነው። ሁለተኛው የመልካም አስተዳደር ዘይቤ ብልሃትና ዘዴ፣ በሌላ አነጋገር ተቻችሎና ተከባብሮ በዲሞክራቲክ ሕብረተሰብ ውስጥ አብሮ መኖር ነው። እዚያ ደረጃ ላይ ለመድረስ ለእኛም ለእነሱም ብዙ አመታት ፈጅቶብናል። ያለፈው ምሥጢር እነዲህ ነው። አውሮፓውያኖች-ሮም ቀደም ብላ ከጥበቡ እንደ እኛው ቀምሳለች – ከእንቅልፋቸው የነቁት፣ የግሪኮች ትምህርት የአውሮፓ ገዳም ከገባ ወዲህና የገዳሙ ትምህርት ወደ ዩኒቨርስቲዎች እዚሁ ገዳም ውስጥ ቀስ እያሉ ከተቀየሩ በሁዋላ ነው። የሚታወቀውን ለመድገም- ግሪኮቹ አራት መቶ አመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ነጻ አስተሳሰብን ማራመድና መመራመርን እንዲሁም የሰው ልጆች ነጻነትን ማለት ዲሞክራሲን (ባሪያና ሴቶች ልጆችና የውጭ አገር ሰዎች እኩል መብት አልነበራቸውም እንጂ!) ፈልገው አግኝተው መዳፋቸው ውስጥ አስገብተው በሥልጣኔአቸው ሌሎቹን ቀድመው ለመሄድ ችለዋል። እንዴት ነጻነትን አርነትን ዲሞክራሲን መራመርና መፈላሰፍን ሌሎቹን ቀድመው አገኙ? አግኝተውም በደንብ ሊጠቀሙ ቻሉ? አንዴትስ ግሪኮች ወደቁ? ሮም እንዴት ተነሳች? እሱዋስ እንዴት ወደቀች? ይህ ማደር የሚያስፈልገው አርዕስት ነው። አንድ ግን ለማሳረጊያ ማንሳት የምንፈልገው ነገር ቢኖር እኛ ተከባብረንና ተፋቅረን አብረን በሰላም ለመኖር ከአወቅንበት እንደሚባለው እንደ አውሮፓውያኖች ገና ብዙ አመታት መጠበቅ ሳይሆን ነገ ማድረግ የምንችለው ነገር ነው። ያገኘነው ልምምድ የቀመስናቸው መከራዎች በቂ ትምህርቶች ናቸው። ነጻነትና ነጻ አስተሳሰብ ማለት ደግሞ ማንኛውንም ዓይነት “ባርነትን” አልፈልግም ማለት ነው።እንደ ክርስትና ትምህርት ደግሞ “እኩልነትና ፍቅርን ነጻነትን ወንድማማችነትና … የሚያስተምር ትምህርት የለም።” ግን እሱንም ቢሆን ቫቲካን ሆነች የእኛ ቤተክርስቲያን ወንጌላዊት ሆነች የአሜሪካ የተለያዩ ሴክቶች በደንብ ~ 30 ~