ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 29

በመሆናቸው ነው…“ ይላል። በዚህ መልሱ ከጥፋታቸው እነሱን „ነጻ“ ሊያወጣቸው ፈልጎ አይደለም።የማያውቁት ነገር ውስጥ ገብቶ ያውም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩትን የተለያዩ ሕዝቦችን ማስተዳደር ቀላል ነገር እንዳልሆነ ለማሳየት ብቻ ነው።እሱ እራሱ „…እኔ የማውቀው አለማወቄን ነው“ ሲል አንድ ሰው በየቀኑና በየጊዜው እንደ ችሎታውና ዝንባሌው ማጥናት መመራመር ጥበብና ዕውቀትን መሻት እንጂ እንደ አራቱ መደብ አዋቂ የጨበጥኩት ዕውቀት „በቂ ነው“ ስለዚህ እኔም ጨረቃ ላይ ከንፎ የሚያስወጣውን መንኮራኩር እንዳው በደፈናው እንደ አሜሪካኖቹና እንደ ሩሲያኖቹ „እሠራለሁ“ የሚያግደኝ የለም ብሎ መፎከር እንደማይበቃ ለማሳየት ነው።ሶቅራጠስ አልፎ ሄዶ „ለእራሱ ጥሩ ነገር እሠራለሁ“ ብሎ ግን ደግሞ ባለማወቅ