ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 26

በሰበሰበው ተመክሮው በውይይቱ ላይ በማዳመጡ እጅግ ተደስቶአል። የተደሰተበትም ምክንያት አለው። ይህ ሰው በትውፈት የተደገፈ የተስተካከለ ሕይወት በመምራቱ ነው። ኬፋሎስ የተማሪዎቹን መቁነጥነጥ አይቶ “ከእንግዲህ የተቀረውን እናንተው ተፈላሰፉበት እኔ ግን ለአማልክቶቼ መስዋዕቶቼን ለማደርስ እወጣለሁ” ብሎ ሜዳውን ለፈላስፋዎቹ ለአስተማሪውና ለተማሪዎቹ ለቆ ይወጣል። መልካም ሥራ አንግዲህ -ከንግግሩ ላይ እንደምናየው ፖለቲያም የተባለው መጽሓፍም ላይ ተጽፎ እንደምናነበው- እንደዚህ ዓይነቱ ነገር ነው። ተቃራኒው ደግሞ „ክፋት“ ነው። ክፋትና አጥፊ እርምጃ ምንድናቸው? ኪፋሎስ ሜዳውን ለቆ እንደወጣ የሶፊስቱ ቁንጮ ዋና መሪ ትራሲማኮስ የሚባለው ፖለቲከኛ መድረኩን ተረክቦ „…ጥሩ ነገር መሥራት ማለት እኔን የሚጠቅም ሥራ መሥራት ነው።“ ብሎ ንግግሩን ለተማሪዎች ይከፍታል። „.. በተፈጥሮ ሁሉም የሰው ልጅ እኩል አይደለም። ስለዚህ ጠንካራው ጊዜው የሰጠውን ሓብትና ሥልጣንም ከሌሎቹ ተከላክሎ ለእራሱ ሕልውና መቆየት ሲል ጥዋት ማታ መሥራት አለበት። ሁሉንም ነገር ጠቅልሎ በእጁ ሲያስገባ ብቻ ነው እሱ አርፎ መተኛት የሚችለው። አስፈላጊ ከሆነም ቢቻለው ፈላጭ ቆራጭ -ታይረን መሆን አለበት። ከጠንካራ አመራርና ከጠንካራ ሕብረት አንጻር ስንመለከተውና ስናየው እንደዚህ ዓይነቱ ሥርዓት መኖር ደግሞ ተገቢና ትክክል ነው።“ የሚለውን አስተያየቱን ይሠነዝራል። „ይህማ!… ይህን ማድረግና ይህን እንደ ትክክለኛ አማራጭ ማየት መጪውን የእርስ በእርስ ጦርነትና ግጭት በሕዝብ መካከል በቀጠሮ እንደ ማሳደር ነው። ይህ ከሆነ በገዢና በተገዢዎች መካከል ያለው ጥላቻና ለመተናነቅ መፈለለግ አንድ ቀን መምጣቱ የማይቀር ጉዳይ ነው።“ ~ 26 ~