ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 24

የሚለውን አነጋገር የምንረዳው አንዴ ብቻ ሳይሆን አራት አምስት ጊዜ አገላብጠን ስናየው ብቻ ነው። በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በአሜሪካንና በአውሮፓ በአረብ አገሮችና በቻይና በሕንድ በሩሲያና በጀርመን… በአንድ ዘመን „ጨዋ“ የነበረ ሰው በሌላ ዘመን እንደዚያ አስፈሪ የሆነ “አረመኔ ጦረኛ“ ይወጣዋል። ለምን? በምን ምክንያት ? ለምንድነው በአስተሳሰብ የማይስማሙ ሰዎች ብዙ ቦታ በጭካኔ ተነሳስተው የሚጋደሉት ? ለምንድነው በሌላ አካባቢ ሌሎቹ የተለያዩ አመለካከቶች ቢኖራቸውም የሚስማሙት? ምናልባት በአንዳንዱ አካባቢ ሰይጣኖች ስለጠፉ? በሌላው አካባቢ ሰይጣኖች አለቅጥ ስለ ተራቡ? አንዱ አካባቢ በእግዚአብሔር ስለ ተረገመ ? ሌላው አካባቢ በእሱ ስለተቀደሰ? አንዳዶቹን እግዚአብሔር በጣም ስለ ሚወዳቸው? ሌሎቹን በተቃራኒ ሰይጣን ስለ ሚያፈቅራቸው? ወይስ ለእነሱ አሳልፎ ስለ ሰጣቸው? ወይስ እግዚአብሄር እኛን ለመቅጣት ፈልጎ? ፈጽሞ አይመስለንም። ለነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልስ የምናገኘው ስለ ልቦና ስለ አእምሮ ስለ ነፍስና ስለ ሥጋ…ስለ መንፈስ ደስታና ስለ ሓዘን ስለ ሰው ልጆች ባህሪ „ጠለቅ „ ብለን „ጠጋ“ ብለን ለመመልከት ጥረት ስናደርግ ብቻ ነው። ጥንታዊ ግሪኮች ከዕውቀታቸው ሲያካፍሉን መልሱ ይህን ይመስላል። ሁለት አዛውንቶች ለብዙ አመታት ተለያይተውና ተራርቀው ከሰነበቱ በሁዋላ አንድ ቀን ተገናኝተው ስለ የባጥ የቆጡ ስለ ዓለምና ስለ እግዚአብሔር ስለ መንፈሳዊ ኑሮና ስለ ዓለማዊ ችግሮች ይጫወታሉ። ሁለቱም በሁለት የተለያዩ ነገሮች የታደሉ ናቸው። አንደኛው በስምና በዝና በአካበተው ሐብትና ንብረቱ በመንደሩና በአካባቢው የተከበረ ጥሩ ስም ያተረፈ ትልቅ ሰው ነው። ሁለተኛው ጥበብና በዕቀውት በብሩህ አእምሮው ከአገር ድንበር አልፎ የሚሄድ እሱም እንደ ጓደኛው ትልቅ ስም ያተረፈ አዛውንት ነው። ከዚያም በላይ ~ 24 ~