ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 21

የሞራልና የኤትክ ሕግጋት ጋር የሰው ልጅ ይተዋወቃል። ያ ሕግ እነዚህ ሕግጋት የሠፈሩበት የሙሴ ጽላትም የመጀመሪያው መተዳደሪያ ደንብ ኢትዮጵያ በቀጥታ እንደ ደረሰም በታሪካችን ላይ እንመለከታለን። እሱን ተከትሎ የክርስትና ሃይማኖት አገራችን ይገባል። ለመጀመሪያ ጊዜም በዓለም ላይ የአንድ መንግሥት ሃይማኖት ሁኖ የክርስትና ሃይማኖት በአገሪቱ ይታወጃል። ባህላችን ታሪካችን ሥርዓትና ደንቡ ባህሪያችን በአገራችን የተመሠረበት በአይሁድ በክርስቲያና ሃይማኖት ላይ ነው የሚባለውም ለዚሁ ነው። ይህ አንደኛውን የሥልጣኔ በዚያውም የሰይጣን አመጣጥ መነሻ ታሪክ ነው።-ቅዱስ ቁርኣንም ይህን ቦታ በቅጠሎቹ ላይ ይጠቅሳል ። ሌላው አካባቢ ሌላው ባህልና ሥልጣኔ ሌላ እራሱን የቻለ አተራረክ አለው። ከእኛ ባልራቁት በግብጻዊያን ቤት ከዚህ ለየት ያለ አቀራረብ እንዳለ እናነባለን።በግሪክ አማልክቶችና በጃፓኖች ዘንድ የፍጥረት አጀማመር በሌላ ዓይነት ቀርቦአል። የነፋሱ ንጉሥ ሹ በጥንታዊ ግብጾች አመለካከት እንደ አክንባሎ አናታችን ላይ የተዘረጋው ሰማይ አንድ ቀን ተንኮታኩቶ ወድቆ ዓለምንና የሰውን ልጆች እንዳይጨርስ እሱን ቀጥ አድረጎ እንደ ምሶሶ የያዘው ጀግናው ንጉሥ „ንፋሱ ሹ“ ነው ብለው ያኔ እነሱ ያምኑ ነበር። ሰማይና መሬትም ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩም የእሱ ፈቃድ ብቻውን ወሳኝ ነበር። ሳት ብሎት ይህ ንጉሥ ወይም ተቆጥቶ ወይም ጀርባውን ለማከክ አንድ እጁን መሸከሙን ትቶ ለቀቅ ከአደረገው ሰማዩ ተንኮታኩቶ ወርዶ የሰውን ልጆች ሁሉ -መናገር አያስፈልግምያጠፋዋል ብለው ይህ እንዳይሆን እነሱ ይሰግዱለት ነበር። ተንዶ ሰማዩ ከተሰበረ አማልክቶቹ ከሰማይ ላይ ተንሸራተው ወርደው ከሰዎች ጋር ተደባልቀው ያልታወቀ ችግር በሁለቱ መካከል ይፈጥራሉ ~ 21 ~