ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 19

… እንዴት እንደምንኖር? እንዴትስ መኖር እንደአለብን? ለመኖርና በሕይወት ዘመናችን ምን ምን መሥራት እንደሚያስፈልገን? የትኛው ሥርዓት ውስጥ ብንኖር መንፈሳዊና ምድራዊ ደስታ እናገኛለን ብለን በጭንቅላታችን ተመራምረን እንድንደርስበትና አእምሮአችን እንድንጠቀምበት „…የምርጫ ነጻነት“ አምላክ የሰጠበት ሰዓት ነው ብለው እርምጃውን ብዙ ፈላስፋዎች (ሰለ ሰይጣን ሳይጨነቁ) ይህን ጉዳይ አንስተው በእግዚአብሄር ሥራ ይደነቃሉ። በገነት መናፈሻ ውስጥ ከአሉት ብዙ ዛፎች ውስጥ እግዚአብሔር አዳምንና ሔዋንን „…ከዚህች ከጥበብ ዛፍ አንዲት ፍሬ እንዳትበሉ ከበላችሁ ደግሞ ክፉና ደጉን ታውቃላችሁ…ትሞታላችሁ “ ማለቱ በአንድ በኩል „ ትዕዛዙና ሕጉ እዲከበር“ ማስጠንቀቁ ቢሆንም ይህን ባታደርጉ ደግሞ በሌላ በኩል ትዕዛዙን ከአልሰሙ „ እራሳችሁን ችላችሁ“ አእምሮአችሁን ተጠቅማችሁ በዚህች ምድር ላይ ጥራችሁ ግራችሁ ላባችሁን አንጠፍጥፋችሁ ትኖራላችሁ ብሎ እሱ እራሱ (ገና ከመጀመሪያው) አስጠንቅቆ መልቀቁ ተገቢ ምርጫና የመምረጥ መብት ነው ይላሉ ። እንግዲህ በየትኛው ሥርዓት ውስጥ ለመኖር እንደምንፈልግ ወሳኙ እኛ ነን። የሆነውና የተከሰተው የሁለተኛው መንገድ ነው። ከፍሬው በልተው ዓይናቸው ተከፈተ። እራቁታቸው መሆኑንም አወቁት። ይህ ደግሞ በሌላ ቋንቋ የሥልጣኔ መጀመሪያ ነው። በመጀመሪያ ቅጠል በጥሰው -መጽሓፉ እንደሚለው- ሓፍረታቸውን ሸፈኑ። ቀጥለው ወደ እርሻና ከብት እርባታ ተሰማሩ። ደበሎና ሱፍ ደረቡ። ቆይተው ጥጥ ዘርተው ለቅመው ፈትለው ሸማ ሠርተው አጌጡ። ~ 19 ~