ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 39

ቆይተውም ኮነሬል ጋዳፊ ጥቂት የአፍሪካ „ንጉሦችን ከጋና እና ቤኒን ሰብስበው እራሳቸውን „ንጉሠ ነገሥት „ ብለው ሹመው የአፍሪካን መሪዎች ለእነዚያ አዳዲስ ማርቼዲስ ገዝተው የሚሸልሙት ሰዎች አዲስ አበባ ሲገቡ „…ንጉሣችሁ ሲመጣ እንዴት አይሮፕላን ጣቢያ ድረስ መጥታችሁ አትቀበሉም „ ብለው ተቆጥተዋቸዋል። ኪም ኢል ጆንግ የኮሪያው „የበላይ መሪ“ የሚለውን ቃል ስም እና ዝና ክብርና ወግ ለብቻው ጨብጦ ይዞአል። ልጁም (አልጋ ወራሹም) ተመሳሳይ ጥሪ ወደፊት ይኖረዋል። ግጥም ገጣሚዎች፣ ሞራ ገላጮች፣ ትንቢት ተናጋሪዎች ለሒትለርም ለሞሰለኒም ለሳዳም ሁሴን ለቢንላዲንም „….የእግዚአብሔር ስጦታ“ የሚለውን ሐረግ ፈልገው በዘመናቸው ሰጥተው ሰው እንዲያምንበት አድርገዋል። በኢትዮጵያ አንዱ ዘፋኝ “አቤት ቅንድቡ…” ብሎ ሰውን አስጨፍሮአል። “ክቡር ሊቀ- መንበር አማራጭ የሌለው መሪ ” የሚለው ቃል “ከቀዳማዊት” ጋር አብሮ በአለፉት ዘመናት ከደርግ ዘመን ጊዜ ጀምሮ ተሰምቶአል። አብዛኛዎቹ ይህን የሚሉትና ሰው እንዲያምነው ለማድረግ ጥረት የሚያደርጉ ክፍሎች የፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ክፍል “ካድሬዎች” ናቸው። የሚገርመው ሰዎች ሰዎችን አሳዶ የሚፈጅ ሰው -እንደ ሂትለርና ሞሰለኒ እንደ ስታሊንና እንደ…ያሉትን ሰዎች በጭፍን ተከትለው (በሰሜን ኮሪያ መሪው ሲሞት የግድ ይለቀሳል) እነዚህን ሰዎች„….የሚወዱአቸው“ በምን ምክንያት ነው?..ለምንድነው ጠንካራ ክንድ ለአለው ጨካኝ ሊሆን ይችላል ወይም… አስቸጋሪ ሰው “ሕዝቡ ጭፍን “ድጋፉን የሚሰጠው? „መሪን መውደድ“ ወይም መከተል ጊዜያዊ ነገ ንፋስ የሚመታው አቋም ነው ? ወይስ ቋሚ ነገር? ለምንድነው ሰዎች በአንድ ዘመን አንድን “አደገኛ ሰው” የሚከተሉት በሌላ ጊዜ እሱን “እንደማያዉቁት ሰው” የሚክዱት? ይህ ደግሞ ወደ በአለ ግርማ ሞገሱ ወደ „ካርስማቲክ መሪ“ አመጣጥና ውድቀት ምርምር ይወስደናል። ይህቺ ዓለም ሁሌ አዳዲስ ነገር አምጥታ ታሰደነግጣለች። ወይስ በእኛ ላይ ለመቀለድ ትደግማለች? ምርጫ - አንድን መሪን ለተወሰነ ጊዜ ብቻ መምረጥ እሱ ደግሞ ምንድነው? ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 ~ 39 ~