ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 34

ጋይተዋል። ሲሸሹ በጥይት እንደ አውሬ ታድነዋል። መሮጥ የማይችሉት ተይዘው ታርደዋል። ማን ምን እንዳደረገ በሁዋላ ፍርድ ቤት አንዳንዶቹ ተይዘው ቀርበው ቃላቸውን ሰጥተዋል። ጥላቻውና መዘዘኛው የዘር ልዩነት የተጀመረው በቤልጅጎቹ የከፋፍለህ ግዛ ተንኮልና ሥራ የቅኝ ግዛት ዘመን ነው። ከመሬት ተነስተው እንደፈለጉት በ1920 አጋማሽ ላይ አንተ „ቱሲ“ አንተ ደግሞ „ሁቱ“ ብለው ሰውን በዘር ግንድና በአጥንት ቆጠራ እዚያ ሽንሽነውና ከፋፍለው መታወቂያ ወረቀታቸው ላይ ይህን የዘር መለያ ምልክታቸውን ጽፈው ኑዋሪውን አናክሰው አለያይተዋል። ጣሊያንም በኢትዮጵያ ሞክሮ ሳይሳከለት ቀርቶአል። ይህ ሆን ተብሎ ቀደም ተብሎ የተረጨው መርዝ ሥር ሰዶ ሰውን በሩዋንዳ የዛሬ 20 አመት አፋጅቶአል። አሁን በሩዋንዳ ሕዝቡን በዘር መከፋፈልና በመታወቂያው ወረቀት ላይ „ሁቱ እን ቱሲ“ ብሎ ለይቶ መጻፍ በህግ የሚያስቀጣ በመሆኑ እዚያ ተከልክሎአል። ሁሉም አሁን ረዋንዳ ሩዋንዳዊ ናቸው። በደቡብ አፍሪካም የአንድን ሰው ዘር መታወቂያ ወረቀቱ ላይ መጻፍ እዚያም እንዲከለከል እነ ማንዴላ አድርገዋል። በዘር እና በሃይማኖት በመደብና በከረረ አይዲኦሎጂ መበጣበጥ መጨረሻው ማለቂያ የሌለው ፍጅት ነው። ~ 34 ~