ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ልዩ እትም / ታህሳስ/ጥር 2006 / 01 / 2014 – አዲስ ዓመት | Page 8

የፖለቲካ ቲዎሪና ታሪክ የሰጠቺው ፍርድ እኛ ማን ነን? ኦ! … አንቺ ኢትዮጵያ !„ -በእነዚህ ቃላት ነው ትረካውን እሱ የጀመረው -„… በዓለም ታሪክ ውስጥ ያለሽን ታሪክና ቦታ በደንብ ብታውቂ ኑሮ አንቺም እንደ ጃፓኖቹ በአካባቢሽ ተፈርተሽና ተከብረሽ ትኖሪ ነበር። ግን ምን ይደረጋል ብልሃቱን በደንብ አላወቅሽበትም። ባለማወቅሽም ልጆችሽ ዛሬ በባዕድ አገር መሣቂያና መቀለጃ ሁነዋል። እንደ ታላቁዋ ብርታኒያን ወይም እንደ ሆላንድ አንቺም ንጉሥሺን ወይም ንግሥትሽን ይዘሽ ኮርተሽ እንደ ሌሎቹ እኩል ተገቢውን ቦታሽን ይዘሽ በዓለም ላይ ልጆችሽ ሳይፈሩና ሳይዋረዱ ፊታቸውን አስመትተው መድረኩ ላይ እንደ ጓደኞቻቸው በሆኑና መድረኩ ላይ ኮርተው እነሱ በተውረገረጉልሽ ነበር። ምን ይሆናል አይኖችሽ ሳይታወሩ ታውረው ጨልሞ