ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ልዩ እትም / ታህሳስ/ጥር 2006 / 01 / 2014 – አዲስ ዓመት | Page 4
እንደምናውቀው እኛም እርስ በራሳችን
በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁለቴና
ሦስት ጊዜ „…የደስታና የጤና የፍቅርና የሰላም
ዘመን…ለአንቺም ለአንተም ለእኛም ይሁንልን
ይሁንላችሁ!“ እንደ ደንቡና እንደ ቆየው
ልማዳችን በሥነ-ሥርዓቱ እንባባላለን።
ነጮቹ እንደሚሉት በእርግጥ „እሱ ረስቶን“
ይሆን?
በእርግጥም ይህን ምኞት ማቅረቡና ማሰማቱ
በደንብ ብናስብበት (እንደ እኛ) ዕውነቱን
ለመናገር – ምርቃቱ ቀላል አይደለም- የታደለ
ሕዝብ የለም።
ፍቅሩም ሰላሙም ጤንነቱም (በየአለበት ሰው
ሁሉ በነገር ተሳክሮ ዕብደት ብቻ ስለሆነ)
ይኸው የተባለው ምኞት ሳይደርስልን ከአርባ
አመት በላይ ስንቆጥረው አልፎታል።
አዲሱን ዓመት ቢያንስ ሁለት ጊዜ አብዛኛዎቻችን
ውጭ አገር ያለን ሰዎች እናከብራለን። የገና
በዓልን እንደዚሁ። ፋሲካንና ስቅለትን እነሱንም
እንደዚሁ አከታትለን ሁለት ጊዜ አንዱ
የእኛን ሌላ ጊዜ የአውሮፓን ከተለመደው
የከበረ ሰላምታና ምኞት ጋር አብረን እኩል
እናከብራለን።
„…ኤርትራ
ትገንጠል፣…ኤርትራ
ከአልተገነጠለች፣… ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል
አይደለችም። ስለዚህ ኤርትራ ይኸው በእናንተ
ፈቃድና ምኞት ትገንጠል ብላችሁ ጠይቃችሁ
ተገነጠለች። እኛም ይህ ከሆነ ከእንግዲህ ውጭ
የሚንከራተት የኤርትራ ስደተኛ አይኖርም።
ጦርነቱም ያቆማል። ወደፊትም አይኖርም ብለን
ገምተን ነበር። ግን አሁን እንደምናየውና እንደ
ምንሰማው ሰው በብዛት አገሩን እየጣለ እየወጣ
የስደተኛው ቁጥር በውጭ አገር ጨምሮአል።…
ይባስ ብለችሁ ኦሮሚያ ከአልተገነጠለች
ትላላችሁ። ኦጋዴን ከአልሄደች። አማራ
መንደሩን ለቆ ይውጣ ከማለት አልፋችሁ
ደግሞ የእራሳችሁን ትላልቅ ለም የእርሻ መሬት
ከነጫካውና ከነወንዙ ለባዕድ መንግሥታትና
ነጋዴዎች ለሰባና ዘጠና አመታት ቸብችባችሁ፣
በረሃብ አለቅን ልናልቅ ነው እረ እባካችሁ
ድረሱልን ትላላችሁ። …ምንድነው ለመሆኑ
እናንተ የምትፈልጉት? ለመሆኑ የምትፈልጉትን
በቅጡ ታውቃላችሁ….“ ነጮቹ እንደዚህ እያሉ
በየጊዜው ይጠይቃሉ።
ከሞስሊሙ ሓይማኖት ተከታዮችና ከአረቡ
ሕዝብም ጋር እኩል ትልቁን በዓላቸውን
አብረን „…እንኳን አደረሳችሁ…“ ብለን በጋራ
ተመኝተን በጋራ እናከብራለን።
ወይስ ሌሎቹ እንደሚሉት „ምኞቱ ከልብ
ስለአልሆነ …አልሰማ ብሎን ይሆን?“
ይህን የምንልበት በቂ ምክንያት አለን።
ግን አንድ ቅር የሚልና የሚገርምም ነገር አለ።
እሱም :በየጊዜው ለወዳጅ ለጓደኛ ለዘመድና ለጎረቤት
„…የደስታና የሰላም የፍቅርና የጤና…ዘመን
ይሁንልን“ ብለን የምንመኘው ምኞታችንን
እግዚአብሔር ሰምቶ ለምን እስከ አሁን ድረስ
ለዚያ „በመከራና በሥቃይ ለሚኖረው …ሰላምና
ፍቅር ደስታና ጤና ለጠማውና ለሚናፍቀው
ሕ ዝብና ለእኛም ጭምር መልስ የአልሰጠበት
መልስ የማይሰጥበት ምክንያት ? ማወቁ ዕርዳታ አቅራቢ ነጮቹ የፈለጉትን በየጊዜው
አስቸጋሪ ነው።
ቢሉ፣ይህን ሲሉ ዕውነት አላቸው።
4