2
ውድ አንባቢ!
መቼም በሁሉም ነገር ላይ አንድ ዓይነት አመለካከት በሰው ልጆች ዘንድ እንደ ሌለ ሁላችንም – ይህን ማንሳት አስፈልጊ አይደለም- እናውቃለን።
ግን ደግሞ„ኢትዮጵያ የማን ናት?“ ሲባል ሁሉም የእኔ ናት ሊል ይችላል። እንግዲህ የአገራችን የኢትዮጵያ የፖለቲካ መደብ ፣ በሽታውም መድሓኒቱም፣ እብደቱም ቀና ነገሩም ያለው እዚህቺው ጥያቄ ላይና ለእሱዋም ሁሉ በሚሰጠው መልስ ላይ ነው።
ክፋቱም ጭቃኔውም፣ አረመኔነቱና ርህሩህነቱም፣ የእኔ ብቻ ናት በሚለው መልስ ላይ፣ የተመሰረተ ነው። ሊሆንም ይችላል!
የእኔም፣ የእኛም የሚባለው ንትርኩ፣ ጦርነቱ፣ የውንጅልናው ክሱ፣ ጦርነቱና የክተት ዘመቻው፣… አንጃ፣ …. አድርባይ የሚለው „ጠላትነት“ የሚወለደው፣ የተወለደውም ከዚሁ ጥያቄ እና ከዚያም ከምንሰማውም መልስ ይመስለናል።
ኢትዮጵያ የማን ናት ? የሚለው ጥያቄ ወረድ ብላችሁ እንደምታዩት ኤርትራንም ያካትታል።
ወዴት፣ ወዴት እረ ወዴት? አትበሉ እንጂ ይህ ጥያቄ ጅቡቲንም ይጨምራል። ሱማሌንም ይመለከታል። ሱዳንና ኬንያን፣ ታንዛኒያን አልፎም ሄዶም ምሥራቅ አፍሪካን እንዳለ በሙሉ ያጠቃልላል። ድፍን የአፍሪካን እንድነትንም- ፓን አፍሪካን፣… የእነሱን የአፍሪካውያኖችን አላማና የመጨረሻው ግብ እሱ ስለሆንም- እነሱንም ይጨምራል።
ግን እሩቅ ቦታ ሄደን ከመንከራተታችን በፊት እስቲ በኢትዮጵያ (ኤርትራ በእርግጥ እዚህ ሐሳብ ውስጥ አለችበት) እንጀምር። ኢትዮጵያ ለመሆኑ ዛሬ የማን ናት?
መልካም ንባብ።
ዋና አዘጋጁ
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
_____________________________________________________
ርእስ አንቀጽ