Test Drive April 2015 | Page 23
ከዚያም አስመራጭ ኮሚቴ ተቋቁሞ የየዘርፉ አመራሮች ተሰየሙ፡፡
ሁሉም በተስማማበት ምርጫም አንበሳና ነብር ልማቱን በበላይነት
እንዲመሩ በከፍተኛ ማዕረግ ተሾሙ፡፡ ጦጣ ቀልጣፋና ብልጥ
ስለሆነች የውስጥ ግንኙነትና መረጃ ኮሚቴን እንድትመራ
ተመረጠች፡፡ አያ ዝሆን የጥበቃ፣ ቀጨኔ የአትክልተኛነትና ሥነ
ውበት፣ ተኩላ የአደንና የጫካ ደህንነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሁነው
ሲመረጡ አያ ጅቦ የአደጋ ጊዜ ጥሪና የአዋጅ ነጋሪ ኮሚቴ ተጠሪ
ሆነ፡፡ ከአሁን በኋላ በዚያው በጫካው ውስጥ ካሉ የዱር እንስሳት
ሲበላ የተገኘ ወይም ለመብላት ሙከራ ያደረገ ከፍተኛ ቅጣት
እንደሚቀጣ በህግ ተደነገገ፡፡ ሁሉም ወደየሥራው ገባ፡፡ ጫካውም
ሰላም ሰፈነበት፡፡ የጫካው ልምላሜና ውበትም እየጨመረ ሲመጣ
በታሰበው መልኩ የዱር እንስሳት ከሌላ ጫካዎች መምጣት ጀመሩ፡፡
አዳኞችም ሰላምን በማይረብሽ መልኩ አደናቸውን ቀጠሉ፡፡
የጫካው ፈጣን የሆነ የመልማትና የመዋብ እንዲሁም በውስጡ
ያለው የሰላም ወሬ በዓለም ሁሉ ተሰማ፡፡ የጫካው ዓመታዊ
የእንስሳት ገቢም በፍጥነት እያደገ መጣ፡፡
ይሁንና ከጊዜያት በኋላ በጫካው ውስጥ ችግሮች መፈጠር ጀመሩ፡፡
የደኑ እንስሳት ወሬ ሁሉ ልማቱን ዳር ስለማድረስና ብልጽግናውን
ስለማስቀጠል ሳይሆን ስለ ኮሚቴ አመራሮችና ስለ እነ አያ አንበሳ
ሆነ፡፡ ይህ ሲሰለቻቸውም በሌላ ጫካ ስለሚኖሩ እንስሳት
ማውራቱን ተያያዙት፡፡ አያ ዝሆን “እኔን ያክል ግዙፍ ፍጡር እንዴት
የጥበቃን ኮሚቴ ብቻ እመራለሁ? ከአንበሳ በምን አንሳለሁ? ነብርስ
በምን ይበልጠኛል?” እያለ ማጉረምረም ጀመረ፡፡ ስራውንም ትቶ
በሀሜት ተወጠረ፡፡ እነ ዝንጀሮም “ጦጣ በምን በልጣን ነው
የተሾመችብን? ከነብርስ በምን እናንሳለን? ዛፍ በመውጣት ከሆነ እኮ
ከእኛ በላይ ላሳር ነው፡፡” ማለት ጀመሩ፡፡ አያ ጅቦም በበኩሉ
“ከሁሉም የሚልቅና ከሩቅ የሚሰማ ድምጽ ስላለኝ የልማቱ የበላይ
አመራር መሆን ያለብኝ እኔ ነኝ፡፡ እኔ እያለሁ እንዴት ነብር
ይመራናል?” በማለት በድምፁ ማሰብ ጀመረ፡፡ ሁሉም እራሱን ከፍ
በማድረግና ሌላውን በማጣጣል የሀሜት ስራ ተወጠረ፡፡ እነ አያ
አንበሳና አያ ነብር የሚያወርዱት የልማት እቅድ በተገቢው መልኩ
አልፈጸም አለ፡፡ የዱር እንስሳቱ ሁሉ ለወሬ እንጂ ለሥራ ጊዜ አጡ፡፡
ጥቂቶች ብቻ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ይወጣሉ፡፡ ሌላው ያንኑ እያባዛ
ሪፖርት ያቀርባል፡፡ የጫካው ልማት ግን አልተቋረጠም፡፡ በጥቂት
ቆራጦች ትግል ለውጡ ይቀጥል እንጅ በሚፈለገው መልኩ ግን
አልሆነም፡፡
አንዳንዶቹ ደግሞ ስለጫካው መጥፎ ነገር ብቻ በማውራት ገቢ
ማግኘት ጀመሩ፡፡ መጥፎ ወሬን ብቻ እየመረጠ የሚያዳምጠውም
በዛ፡፡ እነ አያ አንበሳ ምን ደግ ቢሰሩም “ለጥቅማቸው ነው፡፡
ለጫካውና ለ