Test Drive April 2015
ዩኒቨርሲቲ የኤፍ ኤም ሚዲያ ስርጭት ቢኖራቸውም በማህበረሰቡ
የተምሳሌት አቋም
ስነ-ትምህርት የለውጥ መሳሪያ ሊሆን ይገባል
የ
ዘንድ ከነመኖራቸውም የሚያውቅ ጥቂት የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡
በህትመት ሚዲያ ቢሆን የባሰ እንጂ የተሻለ ነገር አይታይም ፡፡
ተምሳሌት መጽሔት ከዚህ በላይ ያነሳናቸውን በትምህርት እና
ሰው ልጅ በመደበኛም ይሁን ኢ-መደበኛ በሆነ ሁኔታ
በማህበራዊ ጉዳይ ላይ ተዛማጅ የሆኑ ጉዳዬችን በማንሳት የተለያዩ
አካባቢውን እየለወጠ ዛሬ በምንገኝበት ደረጃ ላይ የደረስነው
ዓምዶችን በማዘጋጀት፤ በየመስኩ ያሉ ባለሙያዎችን በማሳተፍ
በትምህርት ነው ፡፡ ጥፋትም ሆነ ልማት የሚከናወነው
ውይይቶችን፤ ክርክሮችን በማድረግና መማርያ መድረክ በመፍጠር
በትምህርት ነው ፡፡ መልካሙን ነገር ብቻ አጎልብቶ ጥፋትን
ለማህበረሰብ እና ለሀገር ፋይዳ ያለው ለውጥ እንዲያመጡ የበኩሏን
ማስወገድ የሚያስችል ትምህርት መስክ አልተፈጠረም፤ ወደፊትም
አይፈጠርም ፡፡ የመድሃኒትን ጥቅም መቶ በመቶ ከመድሃኒቱ የጎንዮሽ
ጉዳት ማስወገድ የሚቻልበት ቴክኖሎጂ ላይ አልደረስንም ፡፡ የጨለማና
ብርሃን፤ መኖርና መሞት፤ ሀብትና ድህነት፤ የጽድቅና ኩነኔ ሂደቶች
የዚህ ተምሳሌት ናቸው ፡፡ ዓለም የምትባለው የፍጥረት መኖሪያ
ከተመሰረተች ጀምሮ የነበረ አሁንም ያለ ወደፊትም የሚኖር አውድ
(ኡደት) ነው ፡፡ ይህ ተፈጥሮ ሚዛኗን የምትጠብቅበት ስልት ነው ፡፡
ዛሬ በደረስንበት የቴክኖሎጂ እድገት ዘመን ዘምኖ እና ደርጅቶ
አለመገኘት ከነባራዊው ዓለም ጋር ያለመራመድ የኋላ ቀርነት ብቻ
ሳይሆን ያላዋቂነት መገለጫ ነው ፡፡ የሀገራችን ስረዓት ትምህርት
እድሜው የሚጀምረው ከአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ይሁን እንጂ
በትምህርት ሚ/ር ስርዓት ተበጅቶለት ትምህርትን ለጥቂት የህብረተሰቡ
ክፍል መስጠት የተጀመረው በአጤ ኃ/ሥላሴ የአገዛዝ ዘመን ነው ፡፡
የአንድን ማህበረሰብ በትምህርት ተለውጧል ለማለት ዘመን ተሸጋሪ
የሆነ ወጥነት ያለው የትምህርት ስርዓት ሊኖር እንደሚገባ በመስኩ
የተሰማሩ ባለሙያዎች ይገልጻሉ ፡፡ አንድን ማህበረሰብ ሚዛን ላይ
የምናወጣው በተማረው የሙያ መስክ ለህበረተሰቡ እና ለሃገሩ ያለው
አበርክቶ ነው ፡፡ ቁጥራቸው የበዛ የትምህርት ተቋሞች መገንባትና
ቁጥራቸው የበዛ
የሰው ኃይል ማፍራት እጅግ የተቀደሰ ተግባር
ቢሆንም ፤ ከመጀመሪያ ድግሪ እስከ ሦስተኛ ድግሪ መማር እጅግ
የሚያስከብር የምሁርነት መገለጫ ቢሆንም ፤ ማህበረሰቡን በአንድ
እርምጃ ወደፊት ካላራመደ፤ ከነበረው ነባራዊ የአሰራር ሂደት ጋት እንኳ
ፈቀቅ ካላለ፤ ከተደጋጋሚ ሃገሪቷ በነጮቹ መዝገበ ቃላት ውስጥ ያላትን
የረሃብተኛ ስም የትርጉም ፍቺ ካላስለወጠ ፤ ዛሬም እንደጥንቱ በበሬ
ማረሳችን እርግጥ ከሆነ፤ በየዓመቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተመራቂዎችን
ማፍራት ፋይዳው ምኑ ላይ ሊሆን ነው ሲል ተምሳሌት ያጠይቃል ፡፡
ትምህርት የለውጥ መሳሪያ እንጂ በራሱ ለውጥ አይደለም፤ መማር
ማወቅ መረዳት እንጂ በራሱ ለውጥ አይደለም ፡፡ ማወቅ የለውጥ
የመጀመሪያ እርምጃ እንጂ በራሱ ግብ አይደለም ፡፡
ይህ የለውጥ ግብ ከሚለካባቸው ዘርፈ ብዙ መንገዶች ውስጥ አንዱ
በመማር ማስተማር ሂደት የሚነሱ የምርምር ስራዎችን ከሸልፍ
ማድመቂያነት ይልቅ ለህትመት የሚበቁበትና ችግር ፈቺ የሚሆኑበት፤
በማህበራዊው ህይወት የአኗኗር ዘዬ በባህል፤ በኢኮኖሚ፤ በፖለቲካ
በኪነ-ጥበብ፤ እንዲሁም በመዝናኛ ያሉትን የቀን ተቀን ውሎ በህትመት
እና በብሮድካስት ሚዲያ ሽፋን ተሰጥቶት ሲሰራበት ነው ፡፡ በከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት አንደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡም የአዲስ አበባ
ድርሻ ትወጣለች ፡፡