TEMSALET m jun, 2015 | Page 8
የኔ ሃሳብ
የኔ ሃሳብ
ያለው!
ከድር አህመድ
ከ
አንድ የልብ ጓደኛዬ ጋር የሆድ የሆዳችንን ስንጨዋወት
በወጋችን መሀል “ንቃ ያለው ባርባ ቀኑ ፤ አትንቃ ያለው
ደግሞ ባ`ርባ `መቱም ያንጎላጃል” አለኝና ከመንቃትና
አለመንቃት ጀርባ መሰጠትም እንዳለ በንጽጽር ጠቆም
አደረገኝ ፡፡ መንቃትና አለመንቃት የሚሉትን ጽንሰ ሀሳቦች በውስጤ
ማውጠንጠኑን ተያያዝኩት፡፡ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ምርምር ተቋም
በተዘጋጀ በአንድ የአማርኛ ቋንቋ መዝገበ ቃላት “ነቃ” የተሰኘውን
ቃል ነቄ፤ ንቃተ-ህሊና እያልን ቃላቱን እያራከምን (እያባዛን)
አቻ ትርጉም ብንፈልግለት አንድም ነቃ..ተሰነጠቀ፤ ተተረተረ
የሚለውን አንድም ነቃ.. እንቅልፉን ጨረሰ፤ ባነነ፤ ንቁ፤ ትጉህ፤
ቀልጣፋ ሆነ ጠረጠረ እያልን ጮሌ ድረስ እስከሚለው ድረስ የተለያዩ
ትርጓሜዎችን ሰጥቶታል፡፡
በአጥጋቢ ሁኔታ የተሰጡትን መዝገበ ቃላዊ ፍችዎች ደጋግሜ
ካጤንኩ በኋላ አሁን ባለን የተግባቦት ድባብ ቃሉ ምን አይነት
አውዳዊ ትጓሜ እንዳለው መፈታተሹን ወደድሁና ይቺን መጣጥፍ
ወደ ማሰናዳቱ አመራሁ፡፡ እነሆ ..
መንቃት የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ ከግለሰባዊ ማንነት እስከ ማህረሰባዊ
አብሮነት ምን አንድምታ እንዳለው በተጫባጭ ማየቱ ጠቃሚ ነው ፡
፡ አንድ ሰው አካላዊና ውስጣዊ አቅሙን በሚገባ መረዳት ከቻለ
የመንቃትን የመጀመሪያውን መስፈርት አሟልቷ