TEMSALET m jun, 2015 | Page 6
በልባቸው አኖሩ፡፡
ዶ/ር ሀምሊን አገራቸው ሳሉ በፌስቱላ ህመም
የምትንገላታ እናት ገጥማቸው አታውቅም፡
፡ የህክምና ባለሙያዎች በተደጋጋሚ
እንደሚገለጹት በወሊድ ወቅት በሽንት
ፊኛ እና በማህጸን መካከል የሚከሰተው
በተፈጥሮ ያልነበረ ቀዳዳ ፌስቱላ ይባላል፡፡
በዶ/ር ካትሪን ሀምሊን ሆስፒታል የህክምና
ባለሙያ ከሆኑት ከወ/ሮ ፌቨን ገለጻ መረዳት
እንደሚቻለው በተለይ አንዲት ሴት ለፌስቱላ
ችግር የመጋለጥ እድሏ የሚያይለው አካሏ
የምጥን ጫና ለመቋቋም በሚያስችል መልኩ
ያልጎለበተ እንደሆነ ነው፡፡ በእንዲህ አይነቱ
አሳዛኝ አጋጣሚ ሽሉ በሚያደርሰው ከአቅም
በላይ የሆነ ውጥረት ከላይ በተገለጸው
አኳኋን ሴቲቱ የፌስቱላ ሰለባ ትሆናለች፡
፡ በሌላም በኩል ምንም እንኳን አንዲት
እናት የሚጠበቀውን ያህል አካላዊ ጥንካሬ
ያላት ብትሆንም ሽሉ በትክክለኛው አቅጣጫ
የማይመጣ ከሆነ ለተመሳሳይ ችግር ልትዳረግ
ትችላለች፡፡ የዚህ ህመም ተጠቂ የሆነች እናት
ሽንቷን ለመቆጣጠር ስለማትችል እጅግ የከፋ
ስነ-ልቦናዊ ስብራትና ማህበራዊ መገለል
ይደርስባታል፡፡
በአንድ ወቅት የደረሰው ገጠመኝ እንዲህ
ነበር አንድ የፌስቱላ ሄስፒታል ነርስ በራሱ
ጉዳይ ወደ መንፈሳዊ ቦታ ይጓዛል፤ በሄደበት
ቦታ የገጠመው ግን አንዲት እናት ከ40
ዓመታት በላይ በፌስቱላ ህመም ተሰቃይተው
ራሳቸውን ወደ ህክምና ማዕከል ሳይወስዱ
የፈጣሪ እርግማን እንደደሆነ በማመን ገዳም
ገብተው ቀሪ ህይወታቸውን ይመሩ ነበር ፡
፡ ታዲያ እዚያበራሱ ጉዳይ መንፈሳዊ ቦታ
ላይ የተገኘው ነርስ እርሳቸውን አሳምኖ
ለማሳከም ከ ሁለት ወራት በላይ ነበር የፈጀበት
፤ ምክንያቱም ይህ የፈጣሪ እርግማ ን ነው
5
“
“
የኛ ተምሳሌት
ሰው ስለራሱ ብቻ ሳይሆን
ማህበራዊ ሚዛኑን በጠበቀ
መልኩ ስለሌላውም
እየተጨነቀ እንዲኖር
በሚያስችል መልኩ
የተቃኘውን ኢትዮጵያዊ
አኗኗር ዶ/ር ካትሪን ከልብ
ያደንቁታል
ብለው ላመኑት ሴት እንዴት ተደርጎ በ ሁለት
ቀን የሚፈወስ እጅግ ቀላል ደዌ መሆኑን
ይንገራቸው ፡፡ የሆነውና የተደረገው ግን ይሄ
ነበር እናም ለ40 ዓመታት በፌስቱላ ህመም
ሲሰቃዩ የነበሩት እናት እናታችን በሚሏቸው
ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን የሰለጠነ ነርስ
ፈወሳቸው ፡፡
“ሰው ስለራሱ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ሚዛኑን
በጠበቀ መልኩ ስለሌላውም እየተጨነቀ
እንዲኖር በሚያስችል መልኩ የተቃኘውን
ኢትዮጵያዊ አኗኗር ዶ/ር ካትሪን ከልብ
ያደንቁታል” ወደ እማማ ካትሪን ገድል
ስንመለስ የዘመንን እንቅልፍ እንዳይሆን
እንዳይሆን የምታንቀላፋው ኢትዮጵያን
እንዲህ በቶሎ መቀስቀስ የሚቻል እንዳልሆነ
አበክረው የተረዱ የሚመስሉት ዶ/ር ካትሪን
ገና በጠዋቱ አጥብቀው የታጠቁትን መቀነት
ሳይፈቱ እነሆ ወደ አመሻሹ ዘልቀዋል፡፡ አሁን
ጦር ሀይሎች በመባል በሚታወቀው በቀድሞ
ልእልት ጸ